top of page

ግንቦት 14 2017 - አዩቴ አፍሪካ የውድድር መረሀ ግብር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊከናወን መሆኑም ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • May 22
  • 1 min read

ከ80 በመቶ በላይ ህዝብ ግብርናው ላይ መሰረት ባደረገ ኢኮኖሚ ኑሮውን ይገፋል፡፡


ታዲያ መተዳደሪያ የሆነው የግብርናው ዘርፍ አሁንም ድረስ ከባህላዊ አስተራረስ እና አመራረት ዘዴ መላቀቅ አልቻለም፡፡


ዘርፉ እንዲዘምንም የተለያዩ ተቋማት በየፊናቸው ስራዎችን ሲከውኑ ይታያል፡፡


ከእነዚያም መካከል ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተሰኘ ተቋም አንዱ ነው፡፡


የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍን መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ተቋም አዩቴ አፍሪካ የተሰኘ የውድድር መረሀ ግብር ይከውናል፡፡


ለ3 ተከታታይ ዓመት የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን የሚያግዙ የፈጠራ ሀሳቦችን በማወዳደር ላይ ያተኮረው አዩቴ አፍሪካ የውድድር መረሀ ግብር ዘንድሮ ለ4ተኛ ጊዜ ሊከናወን መሆኑም ተነግሯል፡፡


ውድድሩም ትኩረት የሚያርገው የኢትዮጵያን ግብርና ሊያዘምን የሚችል ማንኛውም የፈጠራ ሀሳብ ያለው ጉዳይ ላይ ነው የተባለ ሲሆን በተለይ ሴት ተወዳዳሪዎችን የሚያበረታታ ነው ተብሎለታል፡፡


አዩቴ አፍሪካ ለ4ተኛ ያዘጋጀውን መረሀ ግብር ላይ ተሳትፈው የውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ 3 የፈጠራ ባለሙያዎች 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከማግኘትም ባለፈ ስራዎቻቸውን የሚጀምሩበት የብድር ሁኔታ እና የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚያመቻች ሄፈር ኢንተርናሽናል ኢትየጵያ ተናግሯል፡፡


ተወዳዳሪዎች ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page