ግንቦት 13 2017 - ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚወጡ የአደጋ መከላከል ቅድመ ትንበያዎችን ወደ ተግባር የመቀየር ችግር አለባት ተባለ
- sheger1021fm
- 8 minutes ago
- 1 min read
ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚወጡ የአደጋ መከላከል ቅድመ ትንበያዎችን ወደ ተግባር የመቀየር ችግር አለባት ተባለ፡፡
ይህ የሚሆነው የተግባር ስራው ብዙ ገንዘብ መመደብን የሚፈልግና ውድም ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡
ይህን ያለው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ወይም ኢጋድ የአየር ጠባይ ትንበያ ትግበራ ማዕከል ነው፡፡
ኢትዮጵያ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን ሙሉ ለሙሉ እንዳትከውን አድርጓታል ተብሏል፡፡
የኢጋድ የአደጋ መከላከል ስራ አስኪያጅ አህመድ አምድይሁን(ዶ/ር) ኢትዮጵያን እና የኢጋድ አባል አገራትን የአየር ሁኔታ በተመለከተ በአመት ሶስት ጊዜ የትንበያ መረጃዎች እና ቅድመ አደጋ መከላከል ማስጠንቀቂያዎችን እናወጣለን ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ በኢኮኖሚ ዝቅ ያሉ አገራት በኢጋድ በኩል የሚወጡ የቅድመ አደጋ መከላከል ማስጠንቀቂያዎችን ከመተግበር አኳያ ክፍተት አለ ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያም ያላት የበጀት አቅም ውስን በመሆኑ ቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን በሚገባ እንዳትከውን አድርጓታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN