top of page

ግንቦት 12 2017 - የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክንያታዊ ያልሆነ የመብራት መጥፋትን አልታገስም አለ፡፡

  • sheger1021fm
  • May 20
  • 1 min read

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጭ መ/ቤቱ ተቆጣጣሪ የሆነው ይኸው ድርጅት የተዘረጋ መስመር ባለመጠገን እና በተለይ በአዲስ አበባ በዛፍ ምክንያት የሚቋረጠው መብራት 47 በመቶ የሚሸፍን ነው ብሏል፡፡

ይህንንም ችግር ለመፍታት ክረምት ከመግባቱ በፊት ለማስተካከል ወደ ስራ ገብቻለሁ ብሏል፡፡


የኢትዮዽያ ኢንቨሰትመንት ሆልዲንግስ በአገልግሎቱ ላይ ከፍተኛ መቆራረጥ እንዳይኖርና አገልግሎት ሰጭውም ያለምክንያት ደንበኞቹን ቅር እንዳያሰኝ የቁጥጥር ስራዬን አበርትቻለሁ ብሏል፡፡

ree

ወሬውን የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ(ዶር) ለሸገር ነግረዋል።


የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጭ መ/ቤቱ ተቆጣጣሪ የሆነው ይኸው ድርጅት ስለ መብራት መጥፋት ምክንያታዊ ያልሆነ ሰበብ አልፈልግም ብሏል።


በሰበብ አስባቡ መብራት በመቆራረጥ ደንበኞቹ ቅር እንዳይሰኙም ለኢትየኦዽያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እቅድ ተነድፎለታል ተብሏል።


ይህንን ጥራት ያለው አገልግሎትም እንዲሰጥ መንገዱን የአኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ያሳየዋል መባሉን ሰምተናል።



ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page