ግንቦት 11 2017 - በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጥላ ስር የተሰበሰቡት ከ40 በላይ የልማትና አምራች ድርጅቶች ዘንድሮ 19 ቢሊየን ብር ገብረዋል ተባለ።
- sheger1021fm
- 2 days ago
- 1 min read
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጥላ ስር የተሰበሰቡት ከ40 በላይ የልማትና አምራች ድርጅቶች ዘንድሮ 19 ቢሊየን ብር ገብረዋል ተባለ።
እነዚህ ድርጅቶች የፋይናንስ ጤንነትቸው ተመርምሮ ጤነኛ መሆናቸው ታውቋል።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጥላ ስር ተሰባስበው የነበሩት እነዚህ ድርጅቶች ከፊሉ ከዓመታት በፊት የፋይናንስ ደህንነት ችግር ያለባቸው ተብለው የሚጠቀሱም ነበሩ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እንደተናገረው እነዚህ ተቋማት በዘንድሮው በጀት ዓመት 19 ቢሊዮን ብር ግብር ከፍለዋል።
በዚህ ጥላ ስር ያሉት ተቋማት ከሞላ ጎደል ሁሉም በኢኮኖሚው የሚያዋጡት ጉልበት ከፍተኛ እንደሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚው ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ነግረውናል።
ከኢትዮዽያ አየር መንገድ፤ ከ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሌሎች ግዙፍ ድርጅቶች ከተሰበሰቡት ገንዘብ ለገንዘብ ሚኒስቴር የሚገባው 40 ሚሊዮን ብር ዘንድሮ እንደተከፈለ ተሰምቷል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/eih/
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comments