top of page

ግለሰቦች ዲጂታል መታወቂያቸውን ትክክለኛነቱ እና ደህንነቱ በተረጋገጠ መልኩ መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዝ አገልግሎት ይፋ ተደረገ።

  • sheger1021fm
  • 10 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 30 2018


ግለሰቦች ዲጂታል መታወቂያቸውን ትክክለኛነቱ እና ደህንነቱ በተረጋገጠ መልኩ መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዝ አገልግሎት ይፋ ተደረገ።


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የደህንነት የዲጅታል ሰርተፍኬት አገልግሎት ስርዓት ተበጅቶለታል፡፡


በዚህም አገልግሎት በፋይዳ ፕሮግራም ስር ለዜጎች የሚሰጠው እያንዳንዱ ዲጂታል መታወቂያ ትክክለኛነት፣ ሊረጋገጥ የሚችል፤ እና ህጋዊ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያስችላል ተብሏል።

ree

ይፋ የተደረገው ዲጂታል ሰርተፍኬት አገልግሎት የሰዎችን የግል መረጃ የመመዝበር እና በሀሰተኛ ስም የሚወጡ መታወቂያዎችን ለመቆጣጠር፣ አመሳስሎ የመስራት የማጭበርበር እና የማንነት መረጃን አላግባብ መጠቀምን ለመከላከልም ይረዳል ተብሎለታል።


የፋይዳ መታወቂያን የጀርባ ክፍል ኪው አር ኮድ በቀላሉ በስልክ ስካን በማስደረግ አጠቃላይ የግለሰቡን ሙሉን መረጃ እና ትክክለኛነት እንዲሁም ህጋዊነቱን በቀላሉ የሚያሳይ የአሰራር ስርአት ነው።


በተጨማሪም መታወቂያውን የሰጠው አካል ማን እንደሆነም በግልፅ ያስረዳል ተብሏል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page