top of page

በአሰሪ እና ሰራተኛ መካካል ያለውን “የጎሪጥ መተያያት” ማስቆም ካልተቻለ ሀገርን ወደፊት ማራመድ ይቸግራል ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 28 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 21/2018


በአሰሪ እና ሰራተኛ መካካል ያለውን “የጎሪጥ መተያያት” ማስቆም ካልተቻለ ሀገርን ወደፊት ማራመድ ይቸግራል ተባለ።


እስካሁን የቀጠለው “የጎሪጥ መተያያት” ሀገሪቱን ወደኋላ አስቀርቷል ተብሏል።


ይህ የተባለው ዛሬ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ አካባቢው ሰላማዊና ምርታማ እንዲሆን ይረዳል በሚል የአሰሪና ሰራተኛ ምክክር የመደራጀት ምጣኔ ተግባር ላይ በአድዋ ሙዚየም ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።


የሰራተኛን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ጥራት ያለው ምርት ለማምረት እና የተሻለ አገልገሎት ለማቅረብ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን የውይይት የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በቢሮው የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አበበ ተቀባ አስረድተዋል።


አሰሪዎች ከሰራተኞቻቸው ጋር ቁጭ ብለው መመካከር አለባቸው የተባለ ሲሆን ይህን ማድረግ ካልተቻለ ጤናማ የስራ ዓውድ መፍጠር ያዳግታል ሲሉ ሀላፊው አቶ አበበ አክለዋል።


አሰሪዎች ሰራተኛውን ማመን መቻል የግድ እንደለባቸው የተናገሩት ባለሙያው ካላመኑ ግን ሰራተኛው የኔነት ስሜት ተሰምቶት እንዳይሰራ ያደርጋል ብለዋል።


አሰሪዎች ከሰራተኛው ጋር ምክክር ማድረግ አለባቸው የተባለ ሲሆን ግልጽነት ለመፍጠር፣ ለመተማመን እና በሁለቱ መካከል ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር ምክክሩ ይረዳል ተብሏል።


የአዲስ አበባ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸው በአሰሪ እና ሰራተኛ መካካል ያለውን "የጎሪጥ መተያያት" ማስቆም ካልተቻለ አገርን ወደፊት ማራመድ ይቸግራል ብለዋል።


አቶ ሚሊዮን በሰራተኛው እና አሰሪው መካካል ያለውን መሰረታዊ የግንኙነት ችግር መቀረፍ አስፈላጊ ሳይሆን ግዴታ ነው ሲሉ ተናግረዋል።


የሁለቱ አካላት ተቀራርቦ መስራት ተቋማትን ለማሳደግ፣ ምርትን ለመጨመር፣ጥራትን ለማሻሻል እና አገርን ተወዳዳሪ ለማድረግ ድርሻው ከፍተኛ ነው ተብሏል።


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page