ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ከሀገር ውስጥ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን በቂ የውሃ ገንዳ ማዘውተሪያዎች ያስፈልጋታል ተባለ::
- sheger1021fm
- 17 minutes ago
- 1 min read
ጥር 20/2018
ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ከሀገር ውስጥ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን በቂ የውሃ ገንዳ ማዘውተሪያዎች ያስፈልጋታል ተባለ::
ይህ የተባለዉ በጅማ ዩንቨርስቲ እየተካሄደ ባለው 10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ነው::
በውድድሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተወክለው የመጡ የውሃ ዋና ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ነው::
ኢትዮጵያ በቂ የሆነ የውሃ ገንዳ ወይንም ማዘውተሪያዎች ቢኖራት በዘርፉ አሁን ካሉት ስፖርተኞችን የበለጠ ማፍራት ትችላለችም ተብሏል::
ይሁንና በቂ ማዘውተሪያዎች ባለመኖራቸው ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እየተቻለ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌደሬሽን ፅ/ት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ተፈሪ ነግረዉናል::
የውሃ ዋና ስፖርተኞች በግላቸው የውሃ ገንዳ ወይም ማዘተሪያዎች ሄደው ልምምድ ለማድረግ ዋጋቸው የሚቀመስ እንዳልሆነ አክለዋል::

አሁን በኢትዮጵያ 50 ሜትር የሚባሉት እና ለውድድር በቂናቸው የሚባሉት የውሃ ገንዳዎች በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሚገኝ ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ደግሞ ጅማ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ በክልል ደረጃ ቢሾፍቱና ኮምቦልቻ ያሉ የውሃ ገንዳዎች እንደሆኑ ሰምተናል::
አሁን ውድድር እየተካሄደበት የሚገኘው የጂማ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ገንዳ አለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ እና አስፈላጊውን ባሟላ መልኩ የተሰራ በመሆኑ ሌሎች ሃገራዊ ውድድሮችንም ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ ነግረዉናል::
ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እና ክልሎች እንዲህ አይነቱን የመወዳደርያ ማዘዉተርያዎች መገንባት አለባቸው ተብሏል::
ይህ እንዳለ ሆኖ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ ቀደም በተደረገ ውድድር በዚህ በዋና ስፖርት ዘርፍ 42 የወርቅ ሜዳሊያዎችን እንዳገኘች ሃላፊው አቶ ሽመልስ ተፈሪ ያስረዳሉ::
ከዚህ በበለጠ ለመስራትና ተወዳዳሪ ሆኖ ለማግኘት መንግስት ያለውን ችግር ተመልክቶ እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል::
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments