top of page

የደመወዝ ማሻሻያው በወቅቱ በሁሉም አካባቢዎች ለምን ተፈጻሚ መሆን እንዳልቻለ ማብራሪያ እንዲሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተጠይቋል፡፡

  • sheger1021fm
  • Nov 21
  • 1 min read

ህዳር 12 2018

 

የደመወዝ ማሻሻያው በወቅቱ በሁሉም አካባቢዎች ለምን ተፈጻሚ መሆን እንዳልቻለ ማብራሪያ እንዲሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተጠይቋል፡፡

 

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህን ጥያቄው የተጠየቀው የሶስት ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለህዘብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ስራ ሰምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡

 

የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄ በንባብ ያቀረቡት ወ/ሮ ጀማነሽ ወ/ሚካኤል የደመወዝ ማሻሻያው መልካም መሆኑን ጠቅሰው ክፍያው እስከ ጥቅምት አጋማሽ እንዲከፈል ቢታዘዝም እስካሁን የደመወዝ ማሻሻያ ያልደረሳቸው አካባቢዎች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

 

ስራ እንዳይስተጓገል በሁሉም ደረጃ ለምን በወቅቱ የደመወዝ ማሻሻያው ተፈጻሚ መሆን አልቻለም? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

 

ለጥያቄዎቹ መልስ የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር  ዶ/ር ጌታቸው በደመወዝ ክፍያው ላይ ለተስተዋለው ችግር ክልሎችን ተጠያቂ አድርጓል።

ree

ጌታቸው (ዶ/ር) ሲመልሱ አስቀድሞ የፌዴራል መንግስት ደመወዝ ማሻሻያ ሊሰራ ሲል የሰራው በቀድሞ መረጃ መሰረት መሆኑን  ተናግረው ማሻሻያ የተሰራው ክልሎች በሰጡን  መረጃ መሰረት ነው ብለዋል።

 

አንዳንድ ክልሎች ማሻሻያው ከተሰራ በኋላ ያንሰናል የሚል ቅሬት በደብዳቤ እና በአካል ማቅረባቸውን ያስረዱት ምክትል ኮሚሽነሩ ከአንዳንድ የክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር በጉዳዩ ላይ ተነጋግናል ችግሩም የእኛ ሳይሆን የእነሱ መሆኑን ተማምነናል ሲሉ ተናግረዋል።

 

ችግር በስፋት የተፈጠረው በቀድሞ ደቡብ ክልል ስር በነበሩ ክልሎች እንደነበሩ አስታውሰው እኛ ማሻሻያ የሰራነው ከሰኔ 2016 ዓ.ም በፊት በቅጥር ላይ ላሉ ሰራተኞች ነው ብለዋል።

 

ከዚያ ወዲያ ለነበሩ ስራተኞች ቅጥር ኮሚሽኑ እንደማይመለከተው ተናግሮ አሁን ያለባቸውንም ችግር በራስ አቅም ይፍቱ ብለዋል ምክትል ኮሚሸነሩ።

 

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ችግሩ ከእኔ ሳይሆን ከክልሎች ስለሆነ ደመወዙ እንዲከፈላቸው የክትትል አደርጋለሁ ሲል ተናግሯል።

 

ያሬድ እንዳሻው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 
 
 

Recent Posts

See All
በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡

ታህሳስ 6 2018 በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ምስራቅ ወለጋ ጉብሰዮ ወረዳ የተመለሱ ከ141 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ ስለተቋረጠባቸው መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ የአካባቢው ቡሣ ጎኖፋ ወይም የእርዳታ ማስተባበሪያ በበኩሉ ድጋፍ እንዲቀጥል ለሚመለከተው የበላይ አካል ባሳውቅም ድጋፍ ግን ሊቀጥል አልቻለም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page