top of page

የካቲት 7፣2016 - አዋሽ ባንክ እና ማስተር ካርድ አዲስ አለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ እና የክፍያ ጌትዌይ አገልግሎትን በጋራ አስጀመሩ

  • Feb 15, 2024
  • 1 min read

በዛሬው ዕለት ሥራ ላይ የሚውለው የአዋሽ አለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ (Awash International Prepaid card) የባንኩ ደንበኞች በፕላስቲክ ካርዱ አማካይነት እንዲሁም ኤቲኤምን በመጠቀም ገንዘብ ወጪ እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል።


ከዚህ በተጨማሪም ደንበኞች በፖስ ማሽን ክፍያ እንዲፈጽሙና በኦንላይን ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ግብይት በየትኛውም ስፍራ ሆነው መፈጸም እንደሚያስችል የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ እና የባንኩ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዮሐንስ መርጋ አስረድተዋል።



ደንበኞች እንደአስፈላጊነቱ የምንዛሪ ቢሮዎች በመቅረብ በካርዱ ላይ በቂ ገንዘብ ማስሞላት ከመቻላቸውም በተጨማሪ ካርዱ ለአለም አቀፍ ክፍያዎች እና ከጉዞ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ተመራጭ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል።


በሌላ በኩል አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋትና በቴክኖሎጂ የታገዘ ሁሉን አቀፍ የባንክ

አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችለውን የማስተር ካርድ ክፍያ ጌት ዌይ አገልግሎትን(MPGS) በቅርቡ የሚያስተዋውቅ ሲሆን፤ አገልግሎቱ በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞባይል መተግበሪያ ወይም ድረ-ገጾችን በመጠቀም የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ያስችላቸዋል ተብሏል።




በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞች የሚፈልጓቸውን ሸቀጦች በኦንላይን ለማዘዝም ሆነ ክፍያ ለመፈጸም እንደሚያግዝ ሲነገር ሰምተናል፡፡


የአዋሽ ባንክ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ ከ18 ዓመት በላይ ላሉ መንገደኞች የተዘጋጀ ሲሆን ካርዱን ለማግኘት ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በቀላሉ እንደ ፓስፖርት፣ ቪዛ እና የበረራ ትኬት ያሉ አስፈላጊ የጉዞ ሰነዶችን ይዘው የምንዛሬ ቢሮ በመገኘት የባንክ አካውንት መክፈት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።


አዋሽ ባንክ ተቀማጩ ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ፣ የሰጠው ብድር ከ172 ቢሊዮን ብር በላይ፣ ጠቅላላ ሀብቱ 260 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል፡፡


ስራ ከጀመረ 29 ዓመታት የሞላው አዋሽ ባንክ በአሁኑ ሰዓት ከ925 በላይ ቅርንጫፎች፣ ደንበኞቹ ደግሞ 11.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን አስረድቷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Recent Posts

See All
በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል።

በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ተመካካሪ፤ ሦስት ንዑሳን አጀንዳዎች ግን ለአስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ መባሉን ነግረውናል። ወደ አስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page