top of page

የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳ ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ መግባባታቸውን የምክክር ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡

  • 4 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 5 2018


የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳ ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ መግባባታቸውን የምክክር ኮሚሽን ይፋ አደረገ፡፡


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡


አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛሉ፡፡




በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካከረ ነው፡፡


በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ለይ ሲመካከሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ተፈራርመዋል ሲል ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡


ይሁንና ኮሚሽኑ ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ወይንም ያቀረቡዋቸውን ምክረ ሀሳቦችን አልዘረዘረም።


የሌሎች አጀንዳ ተመካካሪዎችም በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን የጋራ አድርገው በቃለ ጉባኤዎቻቸው ላይ በመፈራረም ይስማማሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲልም ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ የባህል፣ የኪነ - ጥበብ እና የስፖርት ዘርፍ የአስተዳደር መዋቅር ወጥነት አለመኖር ፣ የመረጃ አያያዝ ችግር እና የሃብት ብክነት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደጎዳው ጥናት አሳየ።

ነሐሴ 5 2018 በኢትዮጵያ የባህል፣ የኪነ - ጥበብ እና የስፖርት ዘርፍ የአስተዳደር መዋቅር ወጥነት አለመኖር ፣ የመረጃ አያያዝ ችግር እና የሃብት ብክነት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደጎዳው ጥናት አሳየ። ባህል እና ስፖርት በፌዴራል እና በክልል ደረጃ እንኳን ወጥ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር እንደሌለው

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page