የካቲት 26 2017 - ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ የተገኙ ከ1,000 በላይ አሽከርከሪዎችን ቀጥቻለሁ'' የአዲስ አበባ ፖሊስ
- sheger1021fm
- Mar 5
- 1 min read
በታጠፈ እና በማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር ሲገለገሉ ተገኙ የተገኙ ከ1,000 በላይ አሽከርከሪዎችን ቀጥቻለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናገረ፡፡
ቁጥራቸው ቀላል የማይባል አሽከርካሪዎች የተቀባ፣ የታጠፈ ፣ የተፋፋቀ፣ የተቆራረጠ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን በመጠቀም ደምብ ሲተላለፉ ቆይተዋል ሲል ፖሊስ አስታውሷል፡፡
አንዳንዶቹ እንደውም ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው ብሏል፡፡
ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ ቁጥጥር 1,587 ተሽከርካሪዎች ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳን ለጥፈው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

የተፋፋቀ፣ የደበዘዘ፣ የታጠፈ እና የማይታይ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ ቁጥር መጠቀም፣ ከሰሌዳ መብራት ውጪ ሌሎች ዓይነቶችን አብረቅራቂ መብራቶችን መጠቀም፣ ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ መለጠፍ እና ሆን ብለው ሰሌዳን አጥፎ መንቀሳቀስ በቁጥጥሩ ወቅት የተገኙ ጥፋቶች ናቸው ሲል ፖሊስ አስረድቷል፡፡
በጥፋት ውስጥ ከተገኙት ውስጥ ኮድ-1 ወይም ታክሲ 216፣ ኮድ-2 ወይም የቤት መኪና 320፣ ኮድ-3 የሆኑ 1,037 እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች 14 መሆናቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ጠቅሷል፡፡
ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል አብዛኛዎቹ የፊት ወይም የኋላ ሰሌዳ ሳይኖራቸው የተገኙ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 633ቱ ደግሞ የተቆረጠ ወይም ለዕይታ ግልጽ ያልሆነ ሰሌዳ ሲጠቀሙ የተገኙና ሰሌዳውን በማይታይ ቦታ ያሰሩ፣ የተሸፈኑና የተለያየ ቀለም የተቀቡ ሰሌዳዎች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r












Comments