top of page

የካቲት 20 2017 - ዳሸን ባንክ ‘’ሸሪክ’’ ሲል በሰየመው ከወለድ ነፃ አገልግሎት ደንበኞቹ  ከ1.2 ሚሊዮን በላይ መድረሳቸውን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Feb 27
  • 1 min read

ዳሸን ባንክ ‘’ሸሪክ’’ ሲል በሰየመው ከወለድ ነፃ አገልግሎት ደንበኞቹ  ከ1.2 ሚሊዮን በላይ መድረሳቸውን ተናገረ።

 

ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) የጀመረበትን 7ተኛ ዓመት ዛሬ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በዋናው መስሪያ ቤት አክብሯል፡፡

 

ዳሽን ባንክ የካቲት 26/2010 ዓ.ም በአንድ መስኮት የጀመረው የወለድ ነፃ አገልግሎት አሁን ላይ ከ80 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎች እና ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎች በመስኮት  አገልግሎት እየሰጠሁ እገኛለሁ ብሏል።

 

ባንኩ በዚህ መዓዘን ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለደንበኞቹ መስጠቱንም አስረድቷል።

 

ዳሸን ባንክ  የሸሪክ የወለድ ነፃ አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 7 ኛ  ዐመት ምክንያት በማድረግ ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ለ31 ለግብረ-ሠናይ ድርጅቶች ሰጥቷል።

 

22 ሚሊዮን ብሩ  ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበው መሆኑን አስረድቷል።

ዳሸን ባንክ በሱማሌ ክልል ለሚገኙ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ 100 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

 

የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት (ሸሪክ) ከሁለት ዓመት በፊት  በባህሬን ማናማ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ ጠንካራ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚሠጥ ባንክ  በሚል ዕውቅና ማግኘቱንም አስታውሷል፡፡

 

ዳሸን ባንክ በአለም አቀፍ ደረጃ የእስላማዊ ፋይናንስ ተቋማቶችን የሂሳብ፣ ኦዲት እና ሸሪዓ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም አባል የሆነ በኢትዮጵያ ብቸኛው የፋይናንስ ተቋም መሆኑንም አስረድቷል።

 

የሸሪክ 7 ኛ ዓመት በዓልም ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ተነግሯል።

 

በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ከደንበኞች ጋር ያለውን ግኑኝነት ለማጥበቅ የሚያግዙ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰሩ ተነግሯል።

 

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 

 

 

 

 

 

 

Commenti


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page