top of page

የካቲት 12 2017 - የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ የማዘመን ፍላጎት አያሳዩም ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Feb 19
  • 1 min read

የፌዴራል የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ የማዘመን ፍላጎት አያሳዩም ተባለ፡፡


በቼክ እና በ #ደብዳቤ መፈረም እንደ ትልቅ ስልጣን የሚቆጥሩ ባለስልጣናትም አሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡


ተቋማቱ የክፍያ ስርዓታችሁን አዘምኑ ሲባሉ ቶሎ ከመቀበል ይልቅ በነበረው አሰራር መቆየትን ይመርጣሉ ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር ነግሮናል፡፡


የገንዘብ ሚኒስቴር ወጪ ለመቀነስ፣ ለቅልጥፍና፣ እና ለግልፀኝነት ይረዳ ዘንድ የመንግስት ተቋማት የክፍያ ስርዓትን በማዘመኑ በብርቱ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

ree

በዚህ ሂደት ግን እየገጠሙ ያሉ ችግሮች መኖራቸውን በገንዘብ ሚኒስቴር የትሬዠሪ እና የመንግስት ሂሳብ መምሪያ ሀላፊ ነጠሩ ወንድወሰን ነግረውናል፡፡


መንግሰስት በብርቱ እየሰራሁበት ነው ያለው ይህ #የዲጂታል_ስርዓት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉትም ሀላፊዋ አስረድተዋል፡፡


በስርዓቱ ትግበራ ወቅት እየገጠሙን ነው ካሏቸው ችግሮች መካከል አንደኛው ተቋማት ቀድሞ ሲሰሩበት ከነበረው አሰራር ጋር ለመላቀቅ ማስቸገራቸው ነው ተብሏል፡፡


በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል በበቂ አለመኖርም ሌላው ስራውን የፈተነው ጉዳይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


ብዙ መስሪያ ቤቶች አዲሱ የክፍያ ስርዓትን ከመጠራጠርና ካለማመን የተነሳ፣ ትላልቅ በመንግስት ደረጃ ለሚፈጸሙ ክፍያዎች ራሱ #አስር_ብር ፣ መቶ ብር እያስተላለፉ ነው እየለመዱት እየመጡ ያሉት ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚፈጸሙ ክፍያዎችን ማዘመን ያስፈልጋል ብላ በህግ አውጥታ ከደነገገች 15 ዓመታት ቢቆጠሩም ዛሬም ሙሉ በሙሉ ለመተግበር እየተቸገረች ነው፡፡


ለመሆኑ ዛሬስ አገልግሎቱን በዘመናዊ መንገድ ለመፈጸም የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ተሟልተዋል ወይ ስንል ወ/ሮ ነጠሩን ጠይቀናቸዋል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page