top of page

ኮሜርሺያል ኖሚኒስ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ፡፡

  • 2 days ago
  • 1 min read

ነሐሴ 2 2018


ኮሜርሺያል ኖሚኒስ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ፡፡



የኮሜርሺያል ኖሚኒስ የሥራ አመራር ቦርድ የኮሜርሺያል ኖሚኒስን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን መገምገሙን ተቋሙ ይፋ አድርጓል፡፡


በ2018 በጀት ዓመት ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከሚያቀርባቸው የሶስተኛ ወገን እና ሌሎች አገልግሎቶች ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስረድቷል፡፡


በዚህም 805 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ምግኘቱን አስረድቷል፡፡


የ2018 በጀት ዓመት የገቢ እና ትርፍ እቅድ አፈጻጸም ከ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ14.34 በመቶ የገቢ እና የ15.4 በመቶ ያልተጣራ ትርፍ ጭማሪ አሳይቷል ብሏል፡፡


በ2018 በጀት ዓመት ከተያዘው የገቢ እና ትርፍ ዕቅድ አኳያ 94.8 በመቶ የገቢ እና 80.4 በመቶ የትርፍ ማሳካቱ ተጠቅሷል፡፡


በተያዘው በጀት ደግሞ ከ9.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ለማትረፍ እቅድ መያዙ ተጠቅሷል፡፡


ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በቀድሞው ሞርጌጅ ባንክ (በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ) ባለቤትነት በ1958 ዓ.ም የተቋቋመ የግል ኩባንያ ሲሆን፤ በሚሰጣቸው ከ13 በላይ የአገልግሎት ዘርፎች ከ45 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት፡፡


ንጋቱ ሙሉ


Recent Posts

See All
የነሐሴ 2 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ በአለም አቀፉ አረጋጊ ሀይል ማዕቀፍ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ልትልክ ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካዊቱ አገር ፓርላማ የዩጋንዳ ወታደሮች በጋዛ በአረጋጊነት እንዲሰማሩ ድምፅ መስጠቱን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ያቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች እቅድ በ

 
 
 
የምግብ የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ዛሬም ኢትዮጵያ መሻገር ያልቻለችው አንገብጋቢ ችግሯ ነው፡፡

ነሐሴ 2 2018 የምግብ የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ዛሬም ኢትዮጵያ መሻገር ያልቻለችው አንገብጋቢ ችግሯ ነው፡፡ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን ለመከተል ከምግብ ጠረጴዛችን ላይ ይኑሩ የሚባሉት እንደ ስጋ፣እንቁላል እና ወተት ያሉት ምርቶች በዋጋቸው ምክንያት ከብዙዎች ገበታ እየጠፉ ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ጤናማ እና የተመጣጠ

 
 
 
በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ለተፈፀመ በደል መፍትሄ ይሰጣል ፣ በዳዩን ተጠያቂ ያደርጋል ተበዳዩን ይክሳል ተብሎ የታመነበት የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ የማድረግ ስራ ከተጀመረ አመታት አልፈዋል፡፡

ነሐሴ 2 2018 በኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ለተፈፀመ በደል መፍትሄ ይሰጣል ፣ በዳዩን ተጠያቂ ያደርጋል ተበዳዩን ይክሳል ተብሎ የታመነበት የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ የማድረግ ስራ ከተጀመረ አመታት አልፈዋል፡፡ ሂደቱ ቀድሞ ቢጀመርም አካሄዱ ግን እንደ አጀማመሩ መፍጠን አልቻለም የሚሉ አሉ፡፡ ከሀገራዊ ምክክሩ ጎን ለ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page