የኢትዮጵያ ግብርና ለባለመዋዕለ ነዋዮች ሳቢ ያልሆነው ለምንድነው?
- 2 hours ago
- 1 min read
የካቲት 16/2018
ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ቢሆንም ሀብት እውቀታቸው ይዘው ወደዘረፋ የሚቀላቀሉ ባለመዋዕለ ነዋዮች ግን እንደሚፈለገው አይደለም፡፡
ባለሀብቶች ፣ ትራክተር እና ኮምፓልነር ይዘው ግብርና ከመስራት ይልቅ በሪል ስቴት ፣ በሆቴል በመሳሰሉትና በከተማ በሚሰሩ ዘርፎች በስፋት ሲሰማሩ ይታያል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ለባለመዋዕለ ነዋዮች ሳቢ ያልሆነው ለምንድነው?
በሰብል እና ጥጥ የግብርና ዘርፍ ላይ ትሰማርተው የሚሰሩ ባለመዋዕለ ነዋዮች የፋይናንስ ፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት፣ የብድር አቅርቦት አለመመቻቸት ፣ የፀጥታ ችግር እና መሰል ችግሮች በእርሻው ልማት ላይ እየፈተናቸው መሆኑን ያስረዳሉ።
የግብርና ሚኒስቴር አልሚዎቹ ያነሷቸው ችግሮች መኖራቸውን ያምናል።

የግብርና ሚኒስቴርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ዴስክ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረስላሴ ባለመዋዕለ ነዋዮች ሀብታቸውን ፈሰስ አድርገው በእርሻ ልማቱ በበቂ ሁኔታ እንዳይሳተፉ እንቅፋት ናቸው ካሏቸው ጉዳዮች መካከል በቂ የግብርና ኢንሹራንስ አለመኖር ተጠቃሽ ነው።
ይህንን ችግር ለመፍታትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የኢንሹራንስ ቁጥሩን ከፍ የማድረግ ፥ ብድር እንዲመቻችላቸውም ከአበዳሪ ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት እንቅስቃሴዎችም አሉ ብለዋል ።
አቶ አለማየሁ ባለሃብቶች በግብርና ዘርፍ ተሰማርተው የእርሻ ልማቱ ላይ እንዳይሰሩ በርካታ ችግሮችን የጠቀሱልን ቢሆንም በእርሻ ልማት የሚሳተፉ አልሚዎች ግን ከባለፉት ዓመታት አንጻር ቁጥራቸው ከፍ እንዳለ ያነሳሉ ።
መሻሻም መጥቷል ፥ ይኸም የሆነው በዘርፉ የነበሩ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመቃለላቸው ነውም ይላሉ።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments