የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አካባቢውን ሲበክል የቆየውንና ከድርጅቱ የሚወጣውን ፍሳሽ ከ1 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አስተካክላለሁ አለ፡፡
- Apr 14
- 1 min read
ሚያዝያ 6/2018
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለዓመታት አካባቢውን ሲበክል የቆየውንና ከድርጅቱ የሚወጣውን ፍሳሽ ከ1 ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አስተካክላለሁ አለ፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለማህበረሰቡ የእርድ አገልግሎት እየሰጠ በቆየባቸው ባለፉት 70 ዓመታት ከአገልግሎቱ ባሻገር ቄራንና አካባቢውን ሲበክል መቆየቱ በፍርድ ቤት ተረጋግጦበት በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲያስተካክል፤ ካላስተካከለ ከአካባቢው እንዲነሳ የወሰነው ታህሳስ 15 ቀን 2018ዓ.ም ነበር፡፡
ውሳኔውን ተከትሎ ብክለቱን ለማስወገድ ምን እየሰሩ እንደሆነ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ድርጅቱ የእርድ ተረፈ ምርቶችን አቀነባብሮ ለእንሰሳት ምግብነት እያዋለ ነው፤ ብክለቱን እየፈጠረ ያለው ወደ ወንዝ የሚናስወግደው ፍሳሽ ነው ብለውናል፡፡
የፍርድ ውሳኔውን ተከትሎም የከንቲባ ጽህፈት ቤት ለቄራዎች ድርጅትና ለውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አቅጣጫ ተሰጥቷል፤ በዚህም መሰረት የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መስሪያ ቤት የፍሳሽ ማጣሪያ ስራ እንዲሰራ ዲዛይኑን ሰርቶ ለቄራዎች አስረክቧል ብለውናል፡፡
የቄራዎች ድርጅትም ብክለቱን ያስወግዳል የተባለውን የፍሻሽ ማጣሪያ እየሰራሁ ነው ከአንድ ወር በኋላም ስራው ሲጠናቀቅ የድርጅቱ ፍሳሽ እንደቀደመው ወደ ወንዝ የሚለቀቅ መሆኑ ይቀርና በሚሰራው ማጣሪያ ተጣርቶ በአዲስ አበባ ውና ፍሳሽ ማጣሪያ ውስጥ ያልፋል ብለውናል ዋና ስራ አስኪያጁ፡፡
ባለሙያዎች እንደሚሉት ለእርድ ከሚውል አንድ በሬ፣ ወይም በግ ከስጋው ባሻገር ከአጠቃላዩ እስከ 40 በመቶ ያሉ የማይበሉ ተብለው የሚወገዱ የአካል ክፍሎቹ ናቸው፡፡
የቄራዎች ድርጅትም እነዚህ ተረፈ ምርቶች ለእንሰሳት ምግብነት ስለሚቀነባበሩ በማስወገድ ወቅት ብክለት ይፈጠራል ብላችሁ አትስጉ ብሏል፡፡
በተለይ የዶሮ መኖ በስፋት እያመረት ለአዲስ አበባ ከተማና በክልሎች ላሉ ዶሮ አርቢዎች እቀረብኩ ነው የሚለው ድርጅቱ በተጨማሪም ሞራን ለሳሙና ፋብሪካዎች እያቀረበ በመሆኑ ከውጭ የሚገባውን የሞራ ምርት ማስቀረት እንደተቻለም ተጠቅሷል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ብክለት የሚፈጥረው ወደ ወንዝ የምንለቅቀው ፈሳሽ ብቻ ነው ሌሎቹ ውጋጆች ተቀነባብረው ለእንሰሳት ምግብነት እየዋሉ ነው ቢሉም፤ በፍርድ ቤት ክሱ ቀርቦባቸው የነበረው ድርጅቱ በሚለቅቀው በካይ ፈሳሽ፣ጠጣርና ጋዝ የነዋሪው ጤና ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው የሚል ነበር፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
ምንታምር ፀጋው




Comments