top of page

ከጉዞ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያቀላል፣ የቱሪዝም ዘርፉንም ያበረታዋል ተብሎ የተነገረለት የዲጂታል መላ ስራ መጀመሩ ተነገረ።

  • 20 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 19/2018


ከጉዞ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያቀላል፣ የቱሪዝም ዘርፉንም ያበረታዋል ተብሎ የተነገረለት የዲጂታል መላ ስራ መጀመሩ ተነገረ።


“ዛጎል” በሚል መጠሪያ የቀረበው የጉዞ መተግበሪያ ትላንት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ሥራ መጀመሩን ከተላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል ።



“ዛጎል” ሱፐር አፕ በተለይም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጓዦች የአውሮፕላን ጉዞዎችን በቀላሉ በኦን ላይን ማስተናገድ የሚያስችላቸው መድረክ ነው ተብሏል።


መተግበሪያው ተጠቃሚዎች የጉዞ እቅድ ማውጣት ፣ ቦታ መያዝ (Booking) እና ተያያዥ የጉዞ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።


ዛጎል ሁሉንም የጉዞ ፍላጎቶች በአንድ መተግበሪያ መያዝ መቻሉ፣ በ7 የተለያዩ ቋንቋዎች ይሰራል፣ ለአጠቃቀምም ቀላል ነው ተብሏል።


"ዛጎል መተግበሪያ ደንበኞች ካሉበት ሆነው ያለምንም እንግልት የጉዞ ፍላጎቶቻቸውን በሰከንዶች ውስጥ እንዲያሳኩ የሚያስችል ነው" ሲሉ የድርጅቱ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ ወ/ሮ ሙና ሱልጣን መናገራቸው ተጠቅሷል።


ንጋቱ ሙሉ

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page