top of page

የስራ ገበያው እና የተማረ ብቁ የሰው ሀይል

  • sheger1021fm
  • Dec 23, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 14/2018

 

የስራ ገበያው የተማረ እና ብቁ የሰው ሀይል ለማግኘት እየተቸገረ መሆኑን በተደጋጋሚ ይነገራል።

 

ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት ከሚነሱ ችግሮች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት የትምህርት ተቋማት ሲያሰለጥኑ ገበያው በምን ዘርፍ የሰለጠነ ሰው ሀይል ያስፈልገዋል ብለው ተማሪዎቻቸውን አለማሰልጠናቸው እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡

 

ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመማር ሲገቡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በምን ሙያ የሰለጠነ የሰው ሀይል ያስፈልገዋል የሚለውን ሳያጠኑ ነው ቀጥታ የሚገቡት ብለዋል ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያ።

 

ዩኒቨርሲቲዎቹም ቢሆኑ ሀገሪቱ በምን ዘርፍ ምን ያህል የሰለጠነ የሰው ሀይል ያስፈልጋታል የሚለውን ጉዳይ ትኩረት ሲሰጡበት አይስተዋልም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትምህርት እቅድ እና ስራ አመራር ትምህርት ክፍል ባልደረባ ደሞዜ ደገፋ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ 

 


በገፍ ከአንድ ዘርፍ ብቻ ብዙ ተማሪዎችን ስናስመርቅ የስራ አጥ ቁጥሩ እየጨመረ ይመጣል ያሉን ባለሙያው ኢትዮጵያ የተጠናከረ የመረጃ ቋት አለመኖሯ ለዚህ ችግር ዳርጎናል ብለዋል፡፡

 

ከዚህ ቀደም ባሉት ዓመታት ይህንን መሰል አሰራር ባለመከተላችን ትውልድ ጎድተናል ያሉት ዶክተር ደሞዜ ጥፋታችንን በሌላ ትውልድ መድገም የለብንም ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

ለዚህ ደግሞ በኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ ዓመታት ምን ዓይነት ሰልጣኞች በምን የስራ ዘርፍ ያስፈልጉናል የሚለውን መረጃ የሚሰበስብ እራሱን የቻለ ተቋም ሊኖረን ይገባል ያሉን ሲሆን ከአሰልጣኝ ተቋማትም ጋር ተናበው ሊሰሩ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page