የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሶስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የወጣ ደንብ በስራ ላይ እንዲውል ወሰነ፡፡
- 23 hours ago
- 1 min read
ሰኔ 19/ 2018
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሶስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን የወጣ ደንብ በስራ ላይ እንዲውል ወሰነ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን የወሰነው ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡
ሶስቱ ተቋማት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ቤተ መፅሐፍትና ቤተ መዛግብት እና የትምህርት ፈተናዎች አገልግሎት ናቸው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በስብሰባው ሶስቱ ተቋማት ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች በውስጥ ገቢ የሚሸፈኑ ወጪዎችን ከአገልግሎት ተጠቃሚዎች በመሰብሰብ እንዲጠቀሙ የወጣውን ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ከታተመ ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
በተጨማሪም አንድ የብድር ስምምነት እና ኒው ዴቨሎፕመንት ማቋቋሚያ ባንክ ስምምነት ማፅደቂያ ረቂቅ አዋጅን ወደ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መርቷል፡፡
ያሬድ እንዳሻው

