top of page

የሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ።

  • Dec 15, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 6/ 2018


የሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰረዘ።


በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙን ተናግሯል፡፡


የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ ሀገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ ሲሆን ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡


ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ሀገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል ተብሏል።

ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች: -


ከታሀሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ ወዲያውኑ ማቋረጥ ይጠበቅባችኋል ሲል አገልገሎቱ አሳስቧል።


ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች (Deposit Gateways) አገልግሎት መስጠት ማቆም አለባቸውም ተብሏል።


ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው የማቆየት ግዴታ አለባቸው፤ ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ በወንጀል ሕጉ መሰረት ያስቀጣል ተብሏል።


የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ፔይመንት ኢንስቱርመንት ኢሹወርስ እና ፔይመንት ሲስተም ኦፕሬተሮች ከታሕሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ፣ የሁሉም የውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ በመሰረዙ፣ በእናንተ በኩል የውርርድ ድርጅቶቹ የሽያጭ እንቅስቃሴ እንዳያከናውኑ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page