top of page

ክረምት በመጣ ቁጥር የአዲስ አበባ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች በዝናብ ተሞልተው በመገንፈላቸው ለእግረኞችም ይሁን ለተሸከርካሪዎች ወዲህ ወዲያ ሲያስቸግሩ ይታያል፡፡

  • 2 hours ago
  • 2 min read

ነሐሴ 11 2018


ክረምት በመጣ ቁጥር የአዲስ አበባ የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች በዝናብ ተሞልተው በመገንፈላቸው ለእግረኞችም ይሁን ለተሸከርካሪዎች ወዲህ ወዲያ ሲያስቸግሩ ይታያል፡፡


በተለይም እነዚህ መስመሮች በቆሻሻና ሌሎች ቁሶች በመደፈናቸው ውሃውን በአግባቡ ማስወጣት አቅቷቸው በመንገዶች ላይ የሚፈጠረው የውሃ መተኛትና ጎርፍ የሰዎችን እንቅስቃሴ ከማወኩ ባለፈ ለአደጋ ተጋላጭነትንም እየጨመረ መምጣቱ በከተማዋ የሚታይ ችግር ሆኗል፡፡


ለመሆኑ በተመሳሳይ ጊዜ አመት እየጠበቁ የሚገነፍሉት የከተማ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች ጥገናና ጥንቃቄ በሌላ በኩል ክረምቱን ተከትሎ የሚበዛውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ምን ተሰርቷል? ችግሩስ ለምን ከዓመት አመት ዘለቀ ስንል የሚመለከታቸውን ጠይቀናል፡፡


የከተማዋን መንገዶች ከጎርፍ ስጋት ለመቀነስ ሲሰራ ቢቆይም በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ችግሩ አሁንም ይታያል የሚሉት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ እያሱ ሰለሞን ናቸው፡፡


መንገዶች በአገልግሎት ብዛት እንደዚሁም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም ደግሞ በክረምት ወቅት በሚከሰት ጎርፍ ምክንያትም ጉዳት የሚደርስባቸው እንደሆነ ታሳቢ ማድረግ የጥገና ስራዎችን መ/ቤታቸው ሲያከናውን መቆየቱን ይናገራሉ፡፡


በዚህ መሰረት ወደ 145 ኪሎሜትር የሚጠጋ የአስፋልት ጥገና ስራዎችን ባለፉት ጊዜያት አከናውኗልም ብለዋል።


ጎርፍ አደጋ እንዲከሰት ምክንያት ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል የከተማዋ የመሬት አቀማመጥ፣ የነዋሪዎች አሰፋፈር ሁኔታ የወንዝ ዳርቻዎችን ጭምር ተጠግቶ መስፈር በራሱ ለአደጋ መከሰት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው ሲሉም አቶ እያሱ ይጠቅሳሉ፡፡


ስጋቱን ለመቀነስ ከበጋው ጊዜ ጀምሮ ቢሰራም በመንገዶችና በፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮቹ ዙሪያ የሚከናወኑ ህገወጥ ድርጊቶች ግን አሁንም መቀጠላቸው ዋና ችግር ሆኖ ቀጥሏል የሚሉት አቶ እያሱ ይህም መልሶ ጉዳት የሚያመጣው ነዋሪው ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


የጎርፍ አደጋው መጠኑ በጨመረ ቁጥር የሚደርሰው ጉዳትም ከፍተኛ ነውና ይህንን መከላከል ላይ ምን ተሰርቷል ስንል የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሐመድ ጠይቀናል፡፡


ክረምቱ መግቢያ ላይ በአዲስ አበባ ከፍሳሽ ማስወጃዎች እንዲሁም ሌሎች የመንገድ መሰረተ ልማቶች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ህገወጥ ድርጊቶች ብዙ ጊዜ ለጎርፍ አደጋዎች እንዲሁም ለመንገድ ሃብቶች መበላሸት፣ መንገዶቹ ከተገነቡበት እድሜ አንጻር በቂ አገልግሎት ሳይሰጡ እንዲበላሹ በማድረግ በሃገር ሃብትም ላይ ተጨማሪ ጉዳት የሚያደርስ ነው ተብሏል፡፡



ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....


ምህረት ስዩም

Recent Posts

See All
በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ነሐሴ 11 2018 በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በመጪው ረቡዕ እንደሚጸድቁ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page