top of page

በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 11 2018


በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡


በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በመጪው ረቡዕ እንደሚጸድቁ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡


ምክትል ኮሚሽነሯ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተመካካሪዎች ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በራሳቸው እና በሌሎች ቡድኖች ምክረ ሀሳብ ላይ መወያየት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡


እንደ ኮሚሽነሯ ማብራሪያ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ተመካካሪ ቡድኖች የመረጧቸው ተወካዮች በቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ ድግግሞሽ እና ተቃርኖ እንዳይኖር የማጠናከር እና የማጣጣም ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡


ያጣጣሟቸውን ስራዎች ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለ500 ቡድኖች የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡


ስምንቱም ቡድኖች በየራሳቸው አጀንዳዎች ላይ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቡድኖችን ምክረ ሀሳብ ይረዳሉ፤ ባልተሳተፉባቸው ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች ላይም ግብዓት ይሰጣሉ ብለዋል ኮሚሽነሯ በመግለጫቸው፡፡


ግብዓቱም ተሰብስቦ የመጨረሻ ሰነድ ይዘጋጃል፡፡


በዚህም ከነገ በስቲያ ወይም ረቡዕ በ4000 ጉባዔተኞች ይጸድቃል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Recent Posts

See All
በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩት የኢሕአፓ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

ነሐሴ 11 2018 በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩት የኢሕአፓ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡ ​በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮችና አባላት ላይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የ10 ቀ

 
 
 
ስርዓተ ምግብ ላይ በመስራት መቀንጨርን ለመቀነስ፤ ከተቻለ ወደ ዜሮ ለማውረድ እየተሰራ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ይላሉ የስነምግብ ባለሙያዎች፡፡

ነሐሴ 11 2018 ስርዓተ ምግብ ላይ በመስራት መቀንጨርን ለመቀነስ፤ ከተቻለ ወደ ዜሮ ለማውረድ እየተሰራ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ይላሉ የስነምግብ ባለሙያዎች፡፡ በቀበሌ ደረጃ መቀንጨርን ለመከላከል የሚመደቡ ባለሙያዎች የስነ ምግብ ዕውቀት የሌላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ደግሞ በሚፈለገዉል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page