በ769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተመረቁ።
- 2 hours ago
- 1 min read
ነሐሴ 11 2018
በ769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተመረቁ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል።

ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በቶርበን፣ ባቴ፣ ሐሎ ጎባ እና ሐሮ ኦባ ቀበሌዎች ሲሆን፣ በአጠቃላይ 769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው፡፡
አራቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በድምሩ 900 ኪሎ ዋት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላቸው ተብሏል።
በፕሮጀክቱ 7.74 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 10 የማከፋፈያ ትራንስፎርመሮች ተተክለው ሥራ ጀምረዋል።
ማህበራዊ ተቋማትን ጨምሮ ከ5 ሺህ 276 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶቹ፤ በአሁኑ ወቅት በአራቱም ቀበሌዎች ከ844 በላይ አባወራዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን አገልግሎቱን ።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እየተገነቡ ከሚገኙ 8 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ 6ቱ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የፕሮጀክቶቹ ግንባታ የተከናወነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና ብርሃን ተደራሽነት ፕሮግራም አካል ነው።
ንጋት መኮንን
_edited.jpg)

Comments