ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ለውጦች የታሰበላቸው አላማ አላሳኩም ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
ታህሳስ 15/2018
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ለውጦች የታሰበላቸው አላማ አላሳኩም ተባለ፡፡
ይህ የተባለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አተገባበር ዙሪያ በተደረገ ውይይት ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ትምህርት ኮሌጅ ባልደረባ የሆኑት በላይ ተፈራ(ፕ/ር) በዚህ ዙሪያ የመወያያ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
75 ዓመታት ባስቆጠረው የኢትዮጵ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ታሪክ ውስጥ በርካታ ለውጦች ቢደረጉም ያሰቡት ግብ ማሳካት አልቻሉም ብለዋል፡፡

ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋነኞች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ለውጦች ሲደረጉ ከታች እስከላይ ያለው አመራር በትክክል ተረድቶ አይሰራውም፣ ወዲያው የመጣው ለውጥ ውይይት ሳይደረግበት በጥናት ሳይደገፍ ይተገበራል ይላሉ፡፡
ከ75 ዓመት በፊት ሲጠየቅ የነበረው ጥያቄ የኢትዮጵ ከፍተኛ ትምህርት ሀገርኛ አይደሉም የሚል ነበር አሁንም ድረስ ይህ ጥያቄ አለ ሲሉም ያብራራሉ፡፡
በላይ ተፈራ(ፕ/ር) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለውጥ ሲያደርጉ አካባቢውን በተገቢው መንገድ ማየት አለባቸው ሲሉም ነግረውናል፡፡
አሁን የመጡ ቴክኖሎጂዎች ፈጣን ለውጦች እንዲመጣ እያደረጉ ነው፤ ምሁራን ለዚህ ዝግጁ መሆን አለባቸውም ይላሉ ፕሮፌሰር በላይ ተፈራ፡፡
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንደ ከዚህ ቀደሙ ተማሪዎችን በተለመደ የማስተማር ስነዘዴ ማስተማር የለባቸውም ቴክኖሎጂዎች ይህንን ቀይሮታል ከዚህ ቀደም ከነበረው የማስተማር ስነዘዴ የተሻለ አስተምህሮትን መከተል አለባቸው ሲሉም ይመክራሉ፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረጉ ለውጦች በአንድ ጀንበር ለመፈፀም መሞከር የለበትም፣ ውይይቶች ጥናቶች ሊደረጉበትና ለውጡ ትክክለኛ መንገድ መሆኑን በምርምር መረጋገጥ አለበት ይላሉ ፕሮፌሰሩ፡፡
ዩንቨርስቲዎች ቴክኖሎጂን መግፋት አይችሉም ይልቁኑ ይህንን ለመተግበር የሚያስችላቸው ስትራቴጂ እንደ ተቋማ መንደፍ ና መተግበር አለባቸው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








