በቴክኖሎጂ እና በቢሮ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ስራዎች በአግባቡ እየተሰሩ አይደለም ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- 1 day ago
- 1 min read
ሰኔ 19/2018
በቁሳቁስና የቴክኖሎጂ እጥረት ምከንያት በሴቶችና ህፃናት ዙሪያ የታቀዱ ተግባራትን በመስራት ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ።
ሚኒስቴሩ ከUN WOMEN እና ከUNFP ጋር በመተባበር እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን በዋነኝነትም የአካቶ ትግበራን፣ የሥርዓተ ፆታ መረጃ አያያዝና አጠቃቀምን እንዲሁም የአስፈፃሚ ተቋማትንና ባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ተግባራት እንደሚከወኑ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የእዚሁ አካል የሆነ እና ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆኑ የቢሮ ቁሳቁስ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ለፌዴራልና ለ5 ክልል የሥርዓተ ፆታ መዋቅሮች ድጋፍ መደረጉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡
ከአውሮፓ ህብረት እና ከስፓኒሽ ኮርፖሬሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፉ ግምቱ ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስካነር እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ይገኝበታል ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....
ፋሲካ ሙሉወርቅ





Comments