ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አለም አቀፍ የካርድ አገልግሎትቶችን የቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ።
- 18 hours ago
- 2 min read
መጋቢት 12/2018
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አለም አቀፍ የካርድ አገልግሎትቶችን የቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ።
በተጨማሪም የቪዛ ካርዶቹን ለሚጠቀሙ ደንበኞቼ ለአለም ዋንጫ 2026 ጉዞ ወደ ፊፋ በሚል ለሁለት ሰው ሽልማት አሰናድቻለሁ ብሏል።
ለሁለት አሸናፊ ደንበኞቹም አጠቃላይ ወጫቸውን ሸፍኖ የአለም ዋንጫን እንዲካፈሉ የሚያስችላቸው እድል እንዳመቻቸላቸው የተናገረው ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የውድድሩ አሸናፊ ለመሆንም ዛሬ ይፋ የሆነውን የቪዛ ካርዶች ተጠቃሚ ሁኑ ብሏችኋል።
ባንኩ ወደሥራ ያስገባቸው አዳዲስ የካርድ አገልግሎቶች መካከል አንደኛው VISA ክላሲክ ዴቢት ካርድ (በመደበኛና ከወለድ ነጻ) አገልግሎት የሚሰጠው አንደኛው ነው ያሉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደርቤ አስፋው VISA ክላሲክ ፕሪ ፔይድ ካርድም ሌላኛው ለአገልግሎት የሚውለው ነው ብለዋል።

ሶስተኛው የቪዛ አገልግሎት ደግሞ በታላላቅ ደንበኞች አገልግሎት ላይ የሚውለው VISA ፕላቲኒየም ፕሪ ፔይድ ካርድ ነው የተባለ ሲሆን በነዚህ ካርዶች ለሚገለገሉ ደንበኞች የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ መመልከት የሚያስችል የሎተሪ ዕጣ እደላም ተግባራዊ አድርጓል ተብሏል።
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከVISA ጋር በመሆን በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ በተመልካችነት ለመሳተፍ የሚያስችል ዕጣ የሚያስገኘውን "ጉዞ ወደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ 2026" ዘመቻ በይፋ ማስጀመሩን የተናገረ ሲሆን በካርዱ ግብይት ለሚፈጽሙ ደንበኞች የዕጩነት የዕጣ ቁጥር በማደል፣ ዕድለኛ ለሚሆኑ ሁለት ደንበኞች እያንዳንዳቸው አንድ ተጨማሪ ሰው ይዘው ቪዛ፣ የደርሶ መልስ የአየር ትኬት፣ ሆቴልና ምግብን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ያካተተ እጣ እንደሆነ ተናግሯል።
በቪዛ ክላሲክ ዴቢት ካርዶች የተከናወኑ የሀገር ውስጥ ፖስ እና የኢ-ኮሜርስ ክፍያዎች (በመደበኛና በኮፕባንክ አልሁዳ) የሚከናወኑ ግብይቶች፣ በቪዛ ክላሲክ ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚፈጸሙ ዓለም አቀፍና ኦንላይን ክፍያዎች፣ በቪዛ ፕላቲኒየም ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚከናወኑ ፕሪሚየም ዓለም አቀፍ ግብይቶችና በሁሉም ምድቦች የሚከናወኑ ‘ኮንታክትለስ’ ክፍያዎች መፈፀም ለውድድሩ ማሸነፍ ይረዳችኋል ተብላችኋል።
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ካስጀመራቸው ሶስት አዳዲስ የካርድ አገልግሎቶች በተጨማሪም በሰዓት 2,000 ካርዶችን ማስተናገድ የሚችል፣ የግለሰቦችን መረጃ ካርድ ላይ የሚያትም ማሽን ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግሯል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments