ኢትዮጵያ ኬንያና ሶማሊያ በዳዋ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ጥር 22/2018
ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በጋራ ለመጠቀም እና በድርቅ ወቅት የሚከሰቱ ችግርን ለመከላከል ይረዳል በሚል ኢትዮጵያ ኬንያና ሶማሊያ በዳዋ ወንዝ ተፋሰስ ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ እንዳለው የማንዴላ ትሪያንግል በሚል ኢትዮጵያ ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ በሚገኙት መስመር ድርቅ ሲያጋጥም ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በጋራ መጠቀም በሚያስችል ነጥብ ዙሪያ ውይይት መደረጉን ነው፡፡
የዳዋ ወንዝን ተፋሰስ በመከተል በሀገራቱ ውስጥ የልማት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያለመው የሚኒስትሮች ጉባኤ በኬኒያ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡
የዳዋ ወንዝ በድንበር አካባቢ ከ3 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን በድርቅ ወቅት ተፋሰሱ ማገዝ ስለሚችል በወንዙ ላይ ግድቡ በመገንባት ከ2 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ መያዝ በሚያቻልበት ነጥብ ዙሪያ ሚኒስትሮቹ መምከራው ተሰምቷል፡፡
የዳዋ ወንዝ በሶስቱ ሀገራት ደንበሮች አካባቢ ያለውን ማህበረሰብ በችግር ወቅት ለማገዝ ከፍተኛ አቅም አለው የተባለ ሲሆን ግድቡ ቢሰራ ከ12 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ለማልማት ይቻላልም ተብሏል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የአካባቢ ሀገራትን በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ፣ በእንስሳት ሀብት ዝውውርና ሽያጭ ፣ በፀጥታ እንዲሁም በሌሎች መስኮች እንዲተባበሩ እያደረገ ያለ አካባቢያዊ ተቋም ነው፡፡
ኢትዮጵያ ኬኒያዊና ሶማሊያ ካሉበት የማንዴላ ክላስተር በተጨማሪ ሌሎች ጉባኤ ሀገራትን የሚያስተባበሩ የልማት ክላስተሮች በተመሳሳይ መኖራቸውንም ከኢጋድ ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ












Comments