ኢትዮጵያ በኮቪድ እና በአጎአ መታገድ ምክንያት አብዛኛውን በሀገር የምታመርተውን ምርት መሸጥ አልቻለችም፡፡
- sheger1021fm
- Dec 22, 2025
- 1 min read
ታህሳስ 13/2018
ኢትዮጵያ በኮቪድ እና በአጎአ መታገድ ምክንያት አብዛኛውን በሀገር የምታመርተውን ምርት መሸጥ አልቻለችም፡፡
ይህን ተከትሎም መንግስት አምራቾች 50 በመቶውን ለሀገር ውስጥ ፈላጊዎች እንዲሸጡት ወስኗል፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ምርቶች በተለይ በኢ-ኮሜርስ የዲጂታል ገበያ እንዲቀርቡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሸን ምን ዓይነት ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው? መመሪያና ህጋቸውንስ እንዴት እያሻሻሉ ነው?

ለመሆኑ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኤክስፖርት የጥራት ደረጃ የተዘጋጁ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በ'ዘመን ገበያ' ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ለማቅረብም መጀመራቸውን ተከትሎ ቅድሚያ ምን ዓይነት ስራዎች ተፈፅመው ይሆን?
በአለም የንግድ መስመር አንቱ የተባሉ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳትን፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን፣ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን እንዲሁም ሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በዘመን ገበያ ላይም ሆነ ሌሎች የኢ -ኮሜርስ መስመሮች ላይ ለግብይት ሊቀርብ ነው ሲባል ቅድሚያ ከክፍያ ሥርዓት አንፃር ምን ተከናውኗል ተብሎ ይጠየቃል።
የኢ-ኮሜርስ ንግድ የተሻለ እንዲሆን አምራቾችም ምርቱን ፈላጊዎችም ተራርቀው ንግድ ቢዝነስ እንዳይበላሽ ፤ በተለይ አድካሚ የሆነውን የሎጅስቲክስ አሰራር እንዲቀየር ምን ተይዟል?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1












Comments