top of page

ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገች ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ጥር 25/2018

 

ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበች ያለችው ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገች ነው ተባለ፡፡

 

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት አቅም 9750 ሜጋ ዋት፤እየመነጨ ያለው ደግሞ 9730 ሜጋ ዋት  መሆኑ ተነግሯል።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ሲናገሩ እንደሰማነው በኢትዮጵያ ከስድስት አመት በፊት የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በእጥፍ አድጓል።

 

4 ሺህ ሜጋ ዋት ገደማ የነበረው ከታዳሽ የሀይል ምንጭ የኤሌክትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም አሁን 9750 ሜጋ ዋት መድረሱን ተናግረዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት እየመነጨ ካለው ኃይል 9200 ሜጋ ዋቱ ከውሃ፣ 550 ሜጋ ዋት ደግሞ ከንፋስ የሃይል ምንጭ የሚገኝ መሆኑም ተነግሯል።

 

ለሀይል መጠኑ መጨመር ትልቁ ድርሻ የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ መሆኑ ተነግሯል።

 

ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ በአሁኑ ሰዓት የኤሌክትሪክ ሀይል እየገዙ መሆኑንም ጠቁመዋል።

 

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አጠቃላይ ሀብቱ 845 ቢሊየን ብር መድረሱን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

 

በመጪው ዓመት የሀብት መጠኑ ወደ 1 ትሪሊዮን ብር ከፍ እንደሚልም ይጠበቃል ብለዋል።

 

ተቋሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ስድስት ወር ስራው 7.1 ቢሊየን ብር እንዳተረፈም ሰምተናል።

 

በውጭ ምንዛሪ ግኝትም 247 ሚሊየን ዶላር እንዳገኘም ተናግሯል።

 

ተቋሙ ከዚህ በፊት ሀብቱ 99 በመቶ በእዳ ተይዞ ነበር ያሉት ኢንጅነር አሸብር በሀገር በቀል ማሻሻያ እና በተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አሁን ይህ መቀየር ጀምሯል ብለዋል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..  

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page