top of page

ከህግ ውጪ ታስረው የነበሩ ከ1300 በላይ እስረኞችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 17/2018

ከህግ ውጪ ታስረው የነበሩ ከ1300 በላይ እስረኞችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ጋዜጠኞችን ጠርቶ አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት አያያዞችንና ጠቅለል ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡


በኢትዮጵያ ከህግ ውጪ በዘፈቀደ የሚደረግ እስር መኖሩንና ይህም የሰዎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚፃረር በመሆኑ ተደጋጋሚ ውትወታዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡



በዚህም በተያዘው ዓመት ከህግ ውጪ የሆነ እስር የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ያሉት የሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፤ባደረግነው ውትወታ 130 በላይ በዘፈቀደ ታስረው የነበሩ ሰዎችን አስለቅቀናል ብለዋል፡፡


ከኦሮሚያ ክልል 915 ሰዎች ተለቅቀዋል፤በአማራ ክልል 186፣በሶማሌ ክልል 123፣ በጋምቤላ ክልል 66 እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 46 በድምሩ 1336 በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ሰዎች ተለቅቀዋል ተብሏል፡፡


ኮሚሽነሩ አቶ ብርሃኑ በተጨማሪም 122 ሰዎች በዋስተና እንዲለቀቁ ማድረጋቸውንና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እንዲሁ ታስረው የነበሩ 119 ሰዎች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ስለማስረጋቸውም አንስተዋል፡፡


በሌላ በኩል የህግ ታራሚዎች የቀን ፍጆታ በጀት የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ አንዲሆን በተደረገው ውትወታ የተወሰነ ማስተካከያ ቢደረግም የታራሚዎቹ የበጀት ጉዳይ አሁንም ችግር ሆኖ መቀጠሉን ከሃላፊው ሰምተናል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page