አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ አርማ ወይም ሎጎ ይፋ አደረገ።
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
ጥር 22/2018
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ አርማ ወይም ሎጎ ይፋ አደረገ።
ባንኩ ለ18 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን መለያውን ቀይሯል።
የጭረት ምልክትን ይዞ የመጣው አዲሱ የባንኩ ሎጎ የሁሉም ነገር ጅማሬን የሚያመለክት እንደሆነ ተነግሮለታል።
በቤሪ አድቨርታይዚንግ አማካኝነት የተሰራው የባንኩ አዲሱ መለያ ሎጎ በክብ ቢጫ ቀለም ውስጥ ጥቁር ጭረት ያሰፈረ እንደሆነ ተመልከተናል።
የጭረት ምልክትን ይዞ የመጣው አዲሱ የባንኩ ሎጎ የሁሉንም ሀሳብ ጅማሬ ወይም መጀመሪያን የሚያመለክት እንደሆነ ተነግሯል።

ላለፉት አመታት ሲሰራ የቆዬው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ የብራንድ ማንነት ባንኩ ሙሉ ለሙሉ ወደ ለውጥ እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያበስር ነው ተብሏል።
እንደማሳያም ለቀጣዮቹ 3 አመታት በኢንደስትሪው ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ትርጉም ያለው የፋይናንስ አገልግሎት በቴክኖሎጅ ታግዞ አገልግሎት ለመስጠት የሚያበቃውን የስትራቴጅ አቅጣጫ መንደፉን የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ አንስተዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በቴክኖሎጅ የታገዛ አገልግሎትን ለደንበኞቹ መስጠት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የተናገረ ሲሆን አዲሱን አርማ ይፋ ባደረገበት ወቅትም አንበሳ ፕላስ የተሰኘ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን በአዲስ መልክ አሻሽሎ ይፋ አድርጓል።
365 ቅርንጫፍ ያለው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከ6 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉኝ ብሏል።
ባንኩ አሁን ላይ 2.6 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉትም ሲነገር ሰምተናል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7












Comments