አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለሚያስገቡ ደንበኞች የሁለት አመት የክፍያ ስርዓት ማመቻቸቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
- 49 minutes ago
- 1 min read
ሚያዝያ 21/2018
አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለሚያስገቡ ደንበኞች የሁለት አመት የክፍያ ስርዓት ማመቻቸቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለአዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ የሚያስፈልገውን ክፍያ ከፍለው አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ደንበኞች የተዘረጋው ይህ አሰራር እስከ 2 ዓመት በሚደርስ የክፍያ ስርዓት እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል።

ተቋሙ ወደ ስራ ያስገባውን አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የሚችሉትም የነጠላ ፌዝ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው የተባለ ሲሆን የመኖሪያ ቤት እና አነስተኛ ንግድ ቤቶችን ያጠቃልላል ተብሏል።
ይህንን አሰራር የጀመርኩት ጥናትን መሰረት አድርጌ ነው ያለው አገልግሎቱ በርካታ ደንበኞቼ በገንዘብ እጥረት ምክንያት አዲስ ቆጣሪ ማስገባት መቸገራቸውን ጥናቱ አሳይቷል ብሏል።
ደንበኛው የጊዜ ገደብ ክፍያ አገልግሎቱን ተጠቃሚ ለመሆን የቆጣሪ ማስገመቻ ሙሉ ክፍያ መክፈል ያስፈልገዋል የተባለ ሲሆን ከጠቅላላ የማስቀጠያ ክፍያ ላይ 10 በመቶውን መክፈል ይጠበቅበታል ተብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

