አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ ለ8ቱም አጀንዳዎች የተሰጡ የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች ለ4 ሺህ ጉባዔኞች ቀረቡ።
- 4 hours ago
- 1 min read
ነሐሴ 13 2018
አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ ለ8ቱም አጀንዳዎች የተሰጡ የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች ለ4 ሺህ ጉባዔኞች ቀረቡ።
ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ8 አጀንዳዎች፣ ለ96 ንዑሳን አጀንዳዎች እና ለ225 መሪ ጥያቄዎች 476 ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል።
በዚህም በፌደራል ከተሞች አጀንዳ ስር ሲያከራክር ለቆየው የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነት ጉዳይ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ዛሬ ለጉባዔተኛው ተነበዋል።
አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት አካል ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር የሚለው አንደኛው አማራጭ ነው።
የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ "ልዩ ጥቅም" የሚለው ቀርቶ "የጋራ ጥቅም" በሚል ይስተካከል የሚለው ሌላኛው ምክረ ሀሳብ ሆኖ ሰፍሯል።
አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ መሆኗን በተመለከተ ደግሞ ሁለት ምክረ ሀሳቦች ተቀምጠዋል።
እሱም አንደኛ፡ ክልሎች የራሳቸውን ርዕሰ ከተማ መምረጥ እንዲችሉ በፌደራሉ ሕገ መንግስት ይካተት የሚለው አንደኛው ምክረ ሀሳብ መሆኑ ተነግሯል።
አካል፣ ተጠሪ፣ ዋና መቀመጫ እና ርዕሰ ከተማ የሚሉት ቃላት በሕግ ትርጉማቸው እንዲሰፍር ይላል ምክረ ሀሳቡ።
አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ብትሆንም ተጨማሪ ሌሎች ከተሞች ቢጨመሩ፤ የአዲስ አበባን የወሰን ጥያቄ በተመለከተ ደግሞ የወሰን ማካለሉ ስራ እንዲቀጥል የሚሉ ተካተዋል።
የከተማዋን ስያሜዎች በተመለከተ ደግሞ ያሉጉድለቶች ታይተው እንዲስተካከሉ የሚሉት ይገኙበታል።
የድሬዳዋ ከተማን በተመለከተ ደግሞ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስት እንዲሆን እና ሕገ መንግስታዊ እውቅና ባለው ቻርተር ትተዳደር የሚል ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።
ከተማዋ ከምትዋሰናቸው ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ጋር በተያያዘ ደግሞ ስለሚኖራት ግንኙነት በቻርተሩ ይደንገግ።
ከተማዋ የራሷ የሆነ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት ይኑራት የሚለውም ሌላው የተሰጠ ምክረ ሀሳብ ነው።
ሁለቱም ከተሞች በሚወሰኑ የስራ ቋንቋዎች እንዲጠቀሙ የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል።
እነዚህ ዛሬ ለ4 ሺሁ ጉባዔተኛ የተነበቡ ምክረ ሀሳቦች በነገው ዕለት በተመካካሪዎች በጋራ ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ያሬድ እንዳሻው
_edited.jpg)



Comments