top of page

ዳሸን ባንክ 30ኛ የምስረታ ዓመት በዓሉ ማጠቃለያ ላይ ለዲቦራ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን ብር  ሰጠ።

  • 5 days ago
  • 1 min read

ሰኔ 3/2018


ዳሸን ባንክ 30ኛ የምስረታ ዓመት በዓሉ ማጠቃለያ ላይ ለዲቦራ ፋውንዴሽን 30 ሚሊዮን ብር  ሰጠ።


ባንኩ  በዳሸን ዕድል ጨዋታ አሸናፊ ለሆነ ወጣት የቢዋይዲ ሲግል መኪና አበርክቷል።


የባንኩ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን  ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ መርኃ ግብሮች ሲከበር ቆይቷል።


የአከባበር ሥነ ስርዓቱ ማጠቃለያ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት በሸራተን አዲስ ተካሂዷል።



በመርኃ ግብሩ ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የፋይናንስ ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የባንኩ ደንበኞች ተገኝተዋል።


የባንኩን ስያሜ ከማውጣት ጀምሮ የባንኩ ምስረታ ዕውን እንዲሆን ከፍተኛ ዕገዛ ላደረጉት ለሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የዕውቅና እና የማስታወሻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም ለዳሽን ባንክ 11 ባለራዕይ መስራቾች፣ ለቀድሞ የስራ አመራር ቦርድ ኃላፊዎችና ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች፣ አጋር ተቋማት፣ የረዥም ዓመት ደንበኞች እንዲሁም ከዳሸን ባንክ ምስረታ አንስቶ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ላገለገሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡


ዳሽን ባንክ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለዲቦራ ፋውንዴሽን የ30 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡


በሌላ በኩል በዳሽን ሱፐር አፕ በቀረበውና እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ ሽልማቶች በቀረቡበት የዳሽን ዕድል ጨዋታ የዘመናዊ ቢዋይዲ ሲግል የኤሌክትሪክ መኪና አሸናፊ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page