ነሐሴ 4፣2015 - ጆ ባይደንን እገድላለሁ ብሎ ሲዝት የነበረው ግለሰብ እራሱ መገደሉ ተሰማ
- sheger1021fm
- Aug 10, 2023
- 1 min read
የአሜሪካን ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንን እና ሌሎች ሹሞችን እገድላለሁ ብሎ ሲዝት የነበረው እሬግ ሮበርትሰን የተባለ ግለሰብ እራሱ መገደሉ ተሰማ፡፡
ሮበርትሰን ዛቻው በፌስ ቡክ ድረ ገፅ ላይ አስፍሮ እንደነበር ሜይል ኦን ላየን ፅፏል፡፡
ግለሰቡእንዲያዝ የእስር ማዘዣ ወጥቶበት እንደነበር በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ሮበርትሰንየአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ /FBI/ ባልደረቦች ሊይዙት ወደ ቤቱ በመሩበት ወቅት መገደሉ ተሰምቷል፡፡
FBI በዚህ ጉዳይዝርዝር መግለጫ አልሰጠም ተብሏል፡፡
ጆባይደን በፕሬዘዳንትነታቸው የመጀመሪያው የሆነውን የዩታህ ግዛት ጉብኝት እንደሚያደጉ ታውቋል፡፡
የግድያዛቻ መልዕክት አስተላልፎባቸው የነበረው ሮበርትሰንም የዩታህ ነዋሪ ነበር ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments