ነሐሴ 26 2017 - የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ እጥረትና በየጊዜው ዋጋቸው እየተወደደ መሄዱ ለቤት አልሚዎች ፈተና ሆኖ መቀጠሉ ተሰምቷል
- sheger1021fm
- 12 minutes ago
- 1 min read
በሌላ በኩል የቤት ልማትን በተመለከተ የመንግስትና የግል ሽርክና መጀመሩ ለግል ቤት አልሚዎች የተሻለ እድል ፈጥሯል ይላሉ አልሚዎቹ፡፡
መንግስት ለቤት አልሚዎች እና ለዘርፉ ትኩረት መስጠቱን ተከትሎ በዘርፉ የሚሰማሩ የቤት አልሚዎች ቁጥር እንዲጨምርም ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል ያሉን የጊፍት ቢዝነስ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደምም በዘርፉ ይገጥም የነበሩ እንደ ውሃና መብራት ያሉ መሰረተ ልማት ችግሮች ነውም ይላሉ፡፡
ምክትል ስራ አስፈፃሚው በዘርፉ አሁንም ችግሮች ያሉ ቢሆንም የመንግስት የግል አጋርነት በሚለው አሰራር የተቃለሉ ችግሮች አሉ ብለዋል፡፡

ለአብነት እንደ ጊፍት ሪል ስቴት ቦታ ከማግኘት ጀምሮ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችም ጭምር ድጋፎች እንደሚደረጉላቸውም ጠቅሰዋል፡፡
አሁን አሁን በሪል እስቴቱ ዘርፍ በርካታ አልሚዎች እየመጡ ነው የሚሉት አቶ ሰለሞን በሪል ስቴቱ ዘርፉ ጤናማ ያልሆነ የግብይት ስርዓት እንዳለም አልሸሸጉም በሌላ በኩል የግንባታ ግብአቶች እጥረትና ዋጋቸው መወደድ የቤት ልማቱን እየፈተኑ የቀጠሉ ችግሮች ናቸው ተብሏል፡፡
የጊፍት ሪል ስቴት የማርኬቲንግ እና የሽያጭ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርቁ ይርጋ በበኩላቸው ዘመኑ ያፈራቸው የግንባታ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ወደ ሀገር ውስጥ ቢገቡ ዘርፉን ለማሳደግ ያግዛል፣ የቤት ዋጋም ይቀንሳል ፣ግንባታዎችም በፍጥነት ተጠናቀው ለቤት ፈላጊው እንዲደርሱ ያደርጋል ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments