ነሐሴ 26 2017 - የየመን ሁቲዎች መሪ አብዱልመሊክ አል ሁቲ የእስራኤል የአየር ጥቃት አምርረው አወገዙት
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
የየመን ሁቲዎች መሪ አብዱልመሊክ አል ሁቲ በርካታ ሚኒስትሮች በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አምርረው አወገዙት፡፡
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እለት እስራኤል በየመኗ ርዕሰ ከተማ ሰንዓ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ከተገደሉት ሹሞች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትራቸው የነበሩት አህመድ ጋሌብ አል ራሐዊ አንዱ ናቸው መባሉን አልጀዚራ ፅፏል፡፡

በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ሌሎች የሁቲዎቹ ሚኒስትሮች በስም ተለይተው አልተጠቀሱም፡፡
የሁቲዎቹ መሪ እስራኤልን በሚኒስትሮቹ ግድያ ያወገዙት ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ መሆኑ ታውቋል፡፡
እስራኤል የጋዛ የጦር ዘመቻዋን ከጀመረች አንስቶ ሁቲዎቹ ወደ እስራኤል ሚሳየሎች ሲተኩሱ እና አጥቂ ሰው አልባ በራሪ አካላትን /ድሮኖችን/ ሲሰዱባት ቆይተዋል፡፡
እስራኤልም እያሰለሰች በሁቲዎቹ ይዞታ ላይ ከባድ ጥቃቶችን እያደረሰችባቸው ነው፡፡
የየመንን ሰሜናዊ ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎች የኢራን ሁነኛ የጦር እና የፖለቲካ አጋሮች መሆናቸው ይነገራል፡፡
የሁቲዎቹ አለቃ እስራኤል በሚኒስትሮቻቸው ላይ የፈፀመችውን ግድያ እንበቀላለን ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s