ነሐሴ 26 2017 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባው የነበረው የደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ ግንባታው ተቋርጧል ተባለ
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስገነባው የነበረው የደብረ ማርቆስ አየር ማረፊያ ግንባታው ተቋርጧል ተባለ፡፡
አየር ማረፊያውን እየገነባ ያለው መንግስታዊው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በፀጥታው ችግር ምክንያት በቅርቡ ተገድጄ ግንባታውን አቋርጬ ወጥቻለሁ ብሏል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ስራው በመገባደድ ላይ እንደነበር ነግሮናል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በያዘው ፍጥነት ስራውን ቢቀጥል ኖሮ እስከመጭው መስከረም ወር መጨረሻ የአየር ማረፊያ ግንባታው ተጠናቆ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቅ ነበር ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments