top of page

ነሐሴ 24፣2016 - ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የ"እልል ያልኩ ሐበሻ" የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ።

  • sheger1021fm
  • Aug 30, 2024
  • 1 min read

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ የ"እልል ያልኩ ሐበሻ" የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ።


ወጣቱ ድምፂዊ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲያስተዋውቅ ነው የተመረጠው።


በአንድ አልበም እና በተለያዮ ነጠላ ዜማዎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል።


"እልል ያልኩ ሀበሻ" የደመቀ ዝግጅት ትናንት ተካሄዷል።

ree

በ’’ቃና ዌርሀውስ’’ በተዘጋጀው በአይነቱ ለየት ያለ ፐሮግራም የኢትዮያዊያን ባህል፣ ዕሴት፣ ማንነት እና ወግ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል።


በዚህም በምግብ አዘገጃጀት፣ በፋሽን ትርዒት፣ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባሀላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

ree

የዝግጅቱ ዓላማም የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ ምግብ ዝግጅት፣ ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህን ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን እራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ ሲሆን ፕሮግራሙንም ሐበሻ ቢራ አሰናድቶታል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page