top of page

ነሐሴ 24፣2015 - ዳሸን ባንክ ከሁለት የአውሮፓ ተቋምት የ40 ሚሊየን ዶላር ብድር ማግኘቱን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 30, 2023
  • 1 min read


ባንኩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ያገኘው ከእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ('ቢ አይ አይ') እና ከኔዘርላንድሱ የስራ ፈጠራና ልማት ባንክ ከሆነው ኤፍ ኤም ኦ መሆኑ ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡


ሁለቱ ተቋመት እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን ዶላር በድምሩ 40 ሚሊየን ዶላር ብድር ለዳሸን ባንክ ማቅረባቸውን ተነግሯል፡፡


የብድር ገንዘቡ ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርበውን የግብርና ምርት ለማሳደግ እና በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ለማሻሻል ያስችላል ተብሎለታል፡፡


በተለይ በእርሻ ስራ ላይ ለተሰማሩ ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሟላት ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ አስተዋጽኦ ያበረክታል መባሉን ሰምተናል፡፡


ዳሸን ባንክ ብድሩን በማግነቱ ዓይነተ-ብዙ አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያግዘው ጠቅሷል፡፡


ይህም በአመራረት፣ በማጓጓዝ እና በማቀናበር ሂደቶች ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ማቅረብን ይጨምራል ተብሏል፡፡


በዚህ ትብብር 'ቢ አይ አይ' እና 'ኤፍ ኤ ምኦ' የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.ኤ.አ በ2021 አዲስ ባወጣው የውጭ ማንዛሪ ማቀላጠፊያ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ለሚገኝ የፋይናንስ ተቋም በውጭ ምንዛሪ የቀረበ የረዥም ጊዜ ብድር ሲሰጡ የመጀመሪያዎቹ ናቸው ሲል ባንኩ አስታውሷል፡፡

ree

በግብርና ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት የሚቀርብ ፋይናንስ ከአበባ እስከ ቡና እና የቁም ከብት ድረስ የተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችን ለማስተዋወቅ፣ ጥራትን ለማሳደግ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማሟላት እና እሴት ለመጨመር የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡


የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ የ40 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በእጅጉ እነደሚያስፈልግ አንስተው ለተገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አለን" ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡


ዳሸን ባንክ ያገኘው የ40 ሚሊዮን ዶላር ብድር በ3 ዓመት ውስጥ የሚመለስ መሆኑን ባንኩ ነግሯል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

ree


Recent Posts

See All
ህዳር 25 2018 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሁለት ሚኒስትሮችን እና የአንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትን አፀደቀ።

ሹመታቸው በምክር ቤቱ የፀደቀላቸው የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ናቸው። አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሹመው  ስራ የጀመሩት ኀዳር 18 ቀን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page