top of page

ነሐሴ 21፣2016 - UNOPS ለሽሬው ስሁል ሆስፒታል ለጤና መርጃ መሳሪያዎች ግዥ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ማድረጉ ተሰማ

  • Aug 27, 2024
  • 1 min read

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት የተካሄደውን የርስ በርስ ጦርነት ተከትሎ በአለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት መሰረት በሶስተኛ ወገንነት የተመረጠው የመንግስታቱ ድርጅት ተቋም(UNOPS) ለሽሬው ስሁል ሆስፒታል ለጤና መርጃ መሳሪያዎች ግዥ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ማድረጉ ተሰማ፡፡


የአፍሪካ ህብረት ወኪል እንዲሁም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ በማድረግ የአካባቢ ሀገራትን በበላይነት የሚመሩት የተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ መኮንን ከጣሊያን ኤምባሲ ጋር ስለተደረገው ስምምነት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነግረዋል፡፡


በሰሜኑ ጦርነት የደረሰውን የመሰረተ ልማት ውድመት ወደ ቦታው ለመመለስ በወቅቱ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአምስት ክልሎች በአለም ባንክ በጀት መመደቡ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለትግራይ ክልል ስለደረሰውና ስለዋለበት ስራም ወ/ሮ ወርቅነሽ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነግረዋል፡፡


በጦርነት የደረሰው የተቋማት ውድመትን ወደ ቦታው ለመመለስ የትግራይ ክልልን ብቻ UNOPS ሀላፊነትን ሲወስድ በሌሎች አራት ክልሎች የደረሰው ጥፋት ለመስራት የየክልል መንግስታቱ ሀላፊነት መውሰዳቸው ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ...


የኔነህ ሲሳይ

Recent Posts

See All
የሐምሌ 22 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#አሜሪካ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ውስጥ በአፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች ይዞታ ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ የሚገኙ አፍቃሪ ኢራን ታጣቂዎች በድሮን ጥቃት አድርሰውብኛል ስትል እንደነበር አልጀዚራ አስታውሷል፡፡ ሳውዲ ጥቃቱን ከማውገዝ በተጨማሪ መበቀሌ አይቀርም በሚል ዝታ ነበር፡፡ በኢራቆቹ አ

 
 
 
«የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር እንዴት ይሁን? የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነትስ ለማን ይሰጥ? የክልሎች አወቃቀር እንዴት ይሁን እና የጸጥታ ተቋማት እንዴት ገለልተኛ ይሁኑ?» ለሚሉት ጥያቄዎች በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ የተሳተፉ ጉባኤተኞች የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን አስቀምጠዋል።

ሐምሌ 21 2018 «የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር እንዴት ይሁን? የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ባለቤትነትስ ለማን ይሰጥ? የክልሎች አወቃቀር እንዴት ይሁን እና የጸጥታ ተቋማት እንዴት ገለልተኛ ይሁኑ?» ለሚሉት ጥያቄዎች በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ምክክር ላይ የተሳተፉ ጉባኤተኞች የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page