top of page

ነሐሴ 20፣2016 - ባለፈው ሳምንት በየመን የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ

  • Aug 26, 2024
  • 1 min read

ማክሰኞ ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም 25 ኢትዮጵያውያን እና 2 የመናዊያንን አሳፍራ ከጅቡቲ የተነሳችው የስደተኞች ጀልባ ዱባብ አቅራቢያ ልዩ ስሙ ባኒ አል ሃካም አከባቢ ተገልብጣ መስጠሟን በየመን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(አይኦኤም) ዘግቧል።


አደጋውን ተከትሎም 13 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ የተቀሩት 14ቱ ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል ተብሏል።


ከሟቾች መካከል አስራአንዱ ወንዶች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።


የሟቾቹ አስከሬን በዱባብ አከባቢ አልሹራ አቅራቢያ የሚገኘው ባብ-ኤል መንደብ የባህር ዳርቻ ላይ ተገኝቷል።

በስፍራው ያሉ የነፍስ አድን ሰራተኞች የቀሪዎቹን ስደተኞች አካል የማፈላለግ ስራ እስከአሁን እንደቀጠሉ ነው።


በዚህ መስመር በሚያጋጥመው ከባድ ማዕበል ምት እና የጀልባ አቅም ውስንነት ምክንያት በተደጋጋሚ የጀልባ መሰበር፣ መገልበጥ እና መስጠም አደጋ እየደረሰ ይገኛል።


ባለፉት 10 ዓመታት በዚህ ምስራቃዊ መስመር ላይ ብቻ 693 ሰዎች በባህር ላይ የሰጠሙትን ጨምሮ 2,082 የስደተኞች ሞት ተዝግቧል።


በአሁን ወቀት በየመን ያለው አለመረጋጋት እየጨመረ ቢሄድም ከዚህ በተቃራኒ ዜጎች በህገ-ወጥ መንገድ ወደዚህ ስፍራ የሚያደርጉት ጉዞ እየተበራከተ መምጣቱን አይኦኤም(IOM) ዘግቧል።


ንጋቱ ሙሉ

Recent Posts

See All
የነሐሴ 4 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሳውዲ_አረቢያ በሳውዲ አረቢያ ጂዛን በሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከባድ ቃጠሎ ተቅስቅሶ ነበር ተባለ፡፡ በጂዛኑ ማጣሪያ ላይ ቃጠሎ ተቅስቅሶ የነበረው ከባድ ፍንዳታ ከተሰማ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በጁቢየል የተፈጥሮ ጋዝ ማሰናጃ ከተማም ቃጠሎ ተቀስቅሶ ነበር ተብሏል፡፡ የሳውዲ ምንጮች ቃጠሎዎቹ ተቀስቅሰው እ

 
 
 
በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡

ነሐሴ 4 2018 በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት በበኩሉ ሳያጠፋ የምንቀጣው አሽከርካሪ የለም እንዲያውም ሁሉንም ህጎች እናስከብር ብንል የማይቀጣ አሽከርካሪ አይኖርም ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ምህረት ስዩም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page