top of page

ነሐሴ 15፣2015 - የላሙ ወደብ የመጠቀሙ ጥረት ተስፋ እንዳለው ተነገረ


ከጅቡቲ በተጨማሪ የላሙ ወደብን በአማራጭ ወደብነት የመጠቀሙ ጥረት የተሻለ ተስፋ እንዳለው ተነገረ፡፡


የታሰበውየሚሳካ ከሆነ ስራውን የሚያቀላጥፉ ደረቅ ወደቦች በሞያሌ እና በሐዋሳ ለመገንባት መታቀዱ ተነግሯል፡፡


የኢትዮጵያየባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን በተመለከተ ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡


በዓመቱ፤ተቋሙ 5.4 ቢሊየን ብር ከአጠቃላይ ስራው ገቢ ለማግኘት አቅዶ ካሰበው በላይ 6.06 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው ዶ/ር በሪሶ አመሎ ተናገሯል፡፡


ለተቋሙትልቅ መጨናነቅን ፈጥሮ የነበረው የአፈር ማዳበሪያን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት፣ በአጠቃላይ ወጪና ገቢ ምርት ጭነት፣ በመርከብ ምልልስ እና በሌሎቹም ስራዎች በዓመቱ የተሳካ ስራ መስራቱን ተናግሯል፡፡


የባህርትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በ2015 ከተጓጓዘ እቃ ወደ 84 በመቶው በዩኒሞዳል ሥርዓት የተጓጓዘ ነው ብሏል።


ድርጅቱዘግይቶ መግባት የጀመረው የአፈር ማዳበሪያን ወደ አገር ውስጥ ለማጓጓዝ፣ ከወደብ እስከ ዩኒየኖች የማድረስ ስራ ከ4 ቀን በፊት ነሐሴ 11 መጠናቀቁን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡


እስከበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሰኔ 30 ድረስም የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን 85 በመቶ ነበር ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው፡፡


በአጠቃላይለ2015-2016 የእርሻ ዘመን ተገዝቶ የገባው የአፈር ማዳበሪያ መጠን 13 ሚሊየን 975 ሺ 520 ኩንታል መሆኑ ተነግሯል፡፡


ዋናስራ አስፈፃሚው የድርጅቱ አጠቃላይ የዓመቱ ወጪ ወደ 41.8 ቢሊየን ብር ሊደርስ እንደሚችል ቢታቀድም በዓመቱ ያወጣነው ወጪ ግን ካሰብነው በታች 36.6 ቢሊየን ብር ነው ብለዋል፡፡


በአጠቃላይስራው ድርጀቱ 6.06 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቷል ያሉት ሀላፊው በ2016 በጀት ዓመት ገቢውን 6.7 ቢሊየን ብር ለማድረስ አቅዷል ብለዋል፡፡


ከጅቡቲበተጨማሪ ሌሎች ወደቦችን አማራጭ የማድረግ ስራን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ተቋሙ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ የመሳተፍ ውጥን እንዳለውና ከእነዚህም ውስጥ አማራጭ ወደቦችን የማስፋት ስራም እንደሚገኝበት ተናግረዋል፡፡


በተለይየላሙ ወደብን ለመጠቀም የነበረው ድርድር ተስፋ እንደተገኘበትና ይሄም የሚሳካ ከሆነ በሐዋሳ ጥቁር ውሃ አካባቢ እንዲሁም በሞያሌ ተጨማሪ ደረቅ ወደቦች ይገነባሉ ብለዋል፡፡


የላሙወደብ ለአገልግሎት ዝግጁ ስለመሆኑ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ወደቡን በአማራጭነት ለመጠቀም በመንግስት ደረጃ ንግግር እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡



ቴዎድሮስወርቁ


የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Website: t.ly/ShegerFM


YouTube: t.ly/SHEGER


Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


bottom of page