top of page

ነሀሴ 9 2017 - በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 63.12 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Aug 15
  • 1 min read

በ2017 በጀት ዓመት ከኢነርጂ ሽያጭ እና ከሌሎች የገቢ ምንጮች ማለትም ከምሰሶ ሊዝ፣ ከማማከር አገልግሎት፣ ካገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨምሮ የተሰበሰበው ገቢ 63.12 ቢሊየን ብር መሆኑ ተናግሯል።


በተያዘው በጀት አመት ደግሞ ከኢነርጂ ሽያጭ 74.9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅጄ እየሰራሁ ነው ብሏል።


አገልግሎቱ ይህንን ያለው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን እና የ2018 በጀት አመት ዕቅዱን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።


በተጨማሪም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሀይል ስርቆት 2.31 ቢሊዮን ብር ከስሬአለሁ ብሏል።


ይህንን የሀይል ብክነትን ለመከላከል ባደረኩት ቁጥጥር ከ1000 በላይ ግለሰቦች ስርቆት ሲፈፅሙ አግኝቻቸዋለሁ ያለው አገልግሎቱ በቢሊየን የሚቆጠር ብር የባከነ የፍጆታ ሂሳብ ገጥሞኛል ብሏል።

ree

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህንን ኪሳራ ያደረሱበትን ግለሰቦች ህጋዊ ቅጣት እንዲጣልባቸው እያደረግን ነን ያሉት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ካጋጠመን ኪሳራ ውስጥ 1.43 ቢሊዮን ብሩን ለመሰብሰብ ችለናል ብለዋል።


በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 155 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሲናገር ሰምተናል።


ሌላኛው ተቋሙ በ2018 ሊሳራቸው በእቅድ ስለያዛቸው ጉዳዮችም ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን 800 ሺህ ግለሰቦችን አዲስ የሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ በመግለጫው ተናግሯል።


በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት 18,232 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ በጅምላ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመግዛት ማቀዱን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከኢነርጂ ሽያጭም 74.9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱንም ሲናገሩ ሰምተናል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page