ነሀሴ 8 2017 - ከ2.6 እስከ 2.8 ሚልዮን ዓመት ያስቆጠረ የተባለ የሰው ልጅ አዲስ ቅሪተ አካል ተገኘ።
- sheger1021fm
- Aug 14
- 1 min read
በአፋር ክልል ሌዲ ገራዱ አካባቢ ከ2.6 እስከ 2.8 ሚልዮን ዓመት ያስቆጠረ የአውስትራሎፒቴከስ የተባለ የሰው ልጅ አዲስ ቅሪተ አካል ተገኘ።
የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን በአካባቢው ባደረገው ምርምር 13 ጥርሶችን ያገኘ ሲሆን ዝርያውም አዲስ መሆኑን ተነግሯል።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ተገኝቷል ተብሏል።
ግኝቱም በሳይንስ ጆርናል በሆነው ኔቸር ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣ መሆኑን ተጠቅሷል።

አዲሱ አውስትራሎፒቴከስ ይፋዊ ስም እንዳልተሰጠው የጥናት በድን ተሳታፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ኤም ሬክቶር ተናግረዋል።
አዲስ ስም ለመስጠት ተጨማሪ ቅሪተ አካል መገኘት አለበት ምርምሩም ይቀጥላል ብለዋል።

አዲስ የተገኘው አውስትራሎፒቴከስ ዝርያ ከዚህ ቀደም ከተገኘው አውስትራሎፔቲከስ አፋሬንሲስ እንደሚለይ ተነግሯል።
ቅሪት አካሉ በተገኘበት አካባቢ የሰው ልጅ ከሚልዮን ዓመታት በፊት እንደሚኖርበት ጥሩ ማመሳከሪያ ነው ተብሏል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments