ነሀሴ 7 2017 - ወጣቶች በፀጥታና በሰላም ሂደት የሚኖራቸው አቅምና ሚናን በተቋማዊ መንገድ ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Aug 13
- 1 min read
ወጣቶች በፀጥታና በሰላም ሂደት የሚኖራቸው አቅምና ሚናን በተቋማዊ መንገድ ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ በናይሮቢ ኬንያ በተከፈተው የኢጋድ የሰላም እና የፀጥታ ኮንፍረንስ ዙሪያ ወጣቶችን የጉዳዩ ባለቤት ማድረግ በተቋማዊ መንገድ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከአፍሪካ አህጉር 70 በመቶው ወጣት በመሆኑ የሰላምና የፀጥታ ጉዳይን ከወጣቶች ውጪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል፡፡

ያለወጣቶች ሰላምን ማሰብ አይቻላም በተመሳሳይ ያለ ሰላም ወጣቶችን ማሰብም ይከብዳል ሲሉ ዶ/ር ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡
ኢጋድ በሰላም እና በፀጥታ ዙሪያ ላለፉት 40 አመታት ሰላምን በአባል ሀገራት ለማምጣት ብዙ ሰርቷል ይሁንና አሁንም የቀራል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ዶ/ር ወርቅነህ በሰላም እና ፀጥታን ከወጣቶች አንፃር ማየት ለምን ያስፈልጋል ቢባል የወጣቶች ድምፅ ካልታከለበት የእለት ተዕለት የሰላም እና የፀጥታ ስራችን ውጤታማ ስለማይሆን ነው ብለዋል፡፡
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments