ነሀሴ 6 2017 - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካርድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞቹ ያልከፈሉትን የሶስት ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ እያስከፈለ መሆኑን ሰምተናል
- sheger1021fm
- Aug 12
- 1 min read
በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት አዲሱ የ #ተጨማሪ_እሴት_ታክስ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን አዋጅ ተከትሎ የገንዘብ ሚኒስቴር አዋጁን ለማስፈፀም ባወጣው መመሪያ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ መደረግ ተጀምሯል፡፡
ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርገው የነበሩ አገልግሎቶች አንዱ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ነው፡፡
በዚህም መሰረት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የሆነ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች እንዲሁም በሁሉም የንግድና የኢንዱስትሪ ደንበኞች የፍጆታ ሂሳብ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በዚህም የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ባላቸው የፍጆታ መጠን ላይ ተመሥርቶ የሚጠበቅባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ #ክፍያ ከጥር ወር አንስቶ በገዙት ኢነርጂ ወይም ካርድ ሲሞሉ ተግባራዊ መደረጉ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
ነገር ግን የቅድመ ክፍያ ወይም የካርድ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ ይህ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደ ድሕረ ክፍያ ደንበኞች በተመሳሳይ ጊዜ ተግባራዊ መደረግ ቢኖርበትም፤ በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ምክንያት እስከ ታህሣሥ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ ክፍያው ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡
ለዚህ ደግሞ ተቋሙ የካርድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞቹ ያልከፈሉትን የሶስት ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ እያስከፈለ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments