top of page

ነሀሴ 6 2017 - ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በየቀኑ 14,000 ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ እየተመረተ ነው ሲል የግብርና ሚኒስቴር ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 12
  • 1 min read

ይህም ሆኖ ሀገሪቱ ማምረት ከምትችለው የዓሣ መጠን እየተመረተ ያለው ግማሽ ያህሉ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ወሬውን የነገሩን በግብርና ሚኒስቴር የዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሀላፊ ፋሲካ ዳዊት(ዶ/ር) ናቸው፡፡


ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የዓሣ ሀብቱ የሚመራበት ማስተር ፕላን እንዳልነበራት አሁን ግን የ10 ዓመት ማስተር ፕላን መዘጋጀቱን ፋሲል(ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡


በማስተር ፕላኑ ላይ እንደተጠቀሰውም ሀገሪቱ በዓመት 530,000 ቶን ዓሣ ማምረት የሚያስችል አቅም እንዳላት ተጠቅሷል፡፡ አሁን እየተመረተ ያለው ግን 225,000 ቶን መሆኑንን ሰምተናል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 የዓሣ ዝርያዎች መኖራቸው የተነገረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 45ቱ ልክ እንደ ዋሊያ፣ እንደ ቀይ ቀበሮ ብርቅዬ መሆናቸውን ፋሲል (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡


የዓሣ ምርትን ከማሳደግ፣ ህገ ወጥ ተግበራትን ከመከላከል ጋር በተያያዘ የኢጋድ አባል ሀገራት ተመካክረው መፍትሄ ለማምጣት የሚያግዝ ፎርም ለመመስረት አዲስ አበባ ላይ ውይይት ተጀምሯል፡፡


በአዲስ አበባ የተጀመረውና የኢጋድ አባል ሀገራት የዓሣ ሀብት ፎረም እና የዓሣ ሀብት ቁጥጥር ማዕከልን ለማቋቋም ያለመው ውይይት ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚቀጥል ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…….


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page