top of page

ነሀሴ 3 2017 - የተሽከርካሪዎች ብክለት መጠን የሚቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተነገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 9
  • 2 min read

ከተሽከርካሪዎች በሚወጣ በካይ ጋዝ የሚደርስ የአየር ብክለትን ለመከላከል በኢትዮጵያ የሚዘወሩ ተሽከርካሪዎች ብክለት መጠን የሚቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተነገረ፡፡


በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ የተሰናዳው መመሪያ በተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ልቀት ምክንያት የሚደርስ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ተሽከርካሪዎች ይህንን የሚቆጣጠር ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ነው ተብሏል፡፡


መመሪያው ወደ ስራ ሲገባ ተሽከርካሪዎች አመታዊ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ ማረጋገጫ ለማግኘት በተሽከርካሪው ላይ በካይ የጋዝ ልቀትን የሚቀንስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መግጠም ወይም የተሽከርካሪው የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን ከተቀመጠው መስፈርት ያለፈ መሆን እንደሌለበት ተነግሯል፡፡


ይህንን ቴክኖሎጂ አሁን ላይ በኢትዮጵያ በብቸኝነት አስመጥቶ እየሰራ መሆኑን ቲቢኬ ትሬዲንግ ተናግሯል፤ ድርጅቱ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ፈቃድ ያለው የነዳጅ መቆጠቢያና የበካይ ጋዝ ልቀት መቀነሻ መሳሪያን ታይዋን ከሚገኘው ናኖ ቴክኖሎጂ ድርጅት ሞሎቴክ ግሩፕ ወደ ኢትዮጵያ አስመጥቷል ተብሏል፡፡

ree

ድርጅቱ መሳሪያውን ትናንት በስካይላይት ሆቴል አስተዋውቋል፡፡


ከተሽከርካሪዎች በሚወጣ በካይ ጋዝ ምክንያት የሚደርስ የጤና ጉዳትን ለመከላከል በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት የተሽከርካሪዎችን የበካይ ጋዝ መጠን ለመቆጣጠር አስገዳጅ ደረጃ መውጣቱን የሚናገሩት በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ የሆኑት አቶ አሰፋ ሃዲስ ናቸው፡፡


ከሁለት ወራት በኋላ በስራ ላይ እንደሚውል የተነገረው የተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ልቀት መቆጣጠሪያ የተለያዩ ዝርዝር ጉዳዮች መያዙንና ከነዚህም ውስጥ ዓመታዊ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ፈተሻ ለማሟላት የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን ማስተካከልን አስገዳጅ ማድረጉን አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡


መመሪያው ተግባራዊ ሲሆን የአየር ብክለትን ከመቀነስ በተጨማሪ የነዳጅ አጠቃቀምን ያሻሽላል በተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ጉድለት የሚደርስ አደጋን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል፡፡


የበካይ ጋዝ ልቀትን የሚቆጣጠር ግሪን ቴክ የተባለ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት አገልግሎት ላይ እያዋለ ያለው ቲቢኬ ትሬዲንግ ምክትል መስራችና ቴክኒካል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በቀለ ማሞ እንደሚሉት ደግሞ መሳሪያው የተሽከርካሪ በካይ ጋዝ መጠን ከመቀነስ በተጨማሪ የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


እስከ አስር ዓመት ድረስም አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው ብለዋል፡፡


የተሽከርካሪዎችን በካይ ጋዝ ልቀት መጠንን ለመቀነስ ያግዛል የተባለው መሳሪያ ወደ ነዳጅ ማጠራቀሚያ ወስጥ በቀላሉ በማስገባት አገልግሎት ላይ ይውላል የተባለ ሲሆን በካይ የአየር ልቀትን 80 በመቶ እንዲሁም የነዳጅ ፍጆታን ደግሞ በ30 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል፤ መሳሪያው እንደ ተሽከርካሪው የነዳጅ ታንከር መጠን ከ15 ሺህ እስከ 50ሺህ ብር ድረስም ለገበያ መቅረቡን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/5685/


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page