ነሀሴ 27 2017 - በጌዴኦ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የመሬት መሰነጣጠቅ እየተደጋገመ በመሆኑ ነዋሪው ስጋት ውስጥ ነው ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 19 minutes ago
- 1 min read
በ #ጌዴኦ ዞን በቅርቡ የተከሰተውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በአካባቢው የመሬት መሰነጣጠቅ እየተደጋገመ በመሆኑ ነዋሪው ስጋት ውስጥ ነው ተባለ፡፡
በመሬት መንሸራተት አደጋው ከመሬት በታች የተቀበሩ ሰዎችን በሕይወት ለማትረፍና የሞቱትን አስከሬን ለማውጣት የተደረገው ጥረት አለመሳካቱም ተነግሯል፡፡
በደረሰው አደጋ ምክንያት 17 ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ እና እነሱን የማፈላለጉ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የማፈላለግ ሂደቱ ቢቀጥልም የመልካም ምድሩ አቀማመጥ አመቺ ባለመሆኑ አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞናል ሲል የዞኑ ኮሚኒኬሽን ነግሮናል፡፡
አደጋ ምክንያት ከ5,000 በላይ ሰዎች እርዳታ የሚፈልጉ በመሆኑ ከመንግስትም ይሁን ከሌሎች አካላት ድጋፍ እንሻለን ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments